አለም አቀፍ የሴቶች ቀን “የስረአተ ጾታ እኩልነት ለዘላቂ ልማት” እንዲሁም “የእህቴ ጠባቂ ነኝ” በሚል መሪ ቃል በጃፓን ኤምባሲ ተከበረ

የጃፓን ኤምባሲ በኢትዮጵያ በአለም አቀፍ ደረጃ ለአንድ መቶ አስራ አንደኛ ጊዜ ተከብሮ የሚውለውን አለም አቀፍ የሴቶች ቀንን “የስረአተ ጾታ እኩልነት ለዘላቂ ልማት” እንዲሁም “የእህቴ ጠባቂ ነኝ” በሚል መሪ ቃል በኤምባሲው በርካታ ጥሪ የተደረገላቸው አለም አቀፍ ተቋማትና የተለያዩ አምባሳደሮች በተገኙበት ተከበረ፡፡
በፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ በአስተላለፉት መለእክት ኢትዮጵያ የጾታ እኩልነትን የማረጋገጥና ሴቶችን በማህበራዊ፣ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ መስኮች የማብቃት ስራን አጠናክራ እንደምትቀጥል ገልጸዋል፡፡ ሚኒስትሯ አክለው እንደገለጹት የጾታ እኩልነትና ሴቶችን በሁሉም መስክ የማብቃት ስራ መንግስት በተናጥል የሚያከናውነው ተግባር ብቻ እንዳልሆነና የሁሉም አከላት ቅንጅታዊ ተግባር ጭምር መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የጃፓን ኤምባሲ በኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑት ኢቶ ታካኮ በበኩላቸው እንደገለጹት በአለም አቀፍ ደረጃ ሴቶችን መሰረት ያደረገ ጥቃት እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ፣ማህበራዊ መድሎን ማስቆም የሚቻለው በሁሉም አካላት በኩል ያልተቋረጠ ጥረትና ርብርብ ማድረግ ሲቻል መሆኑን ገልጸው የዛሬው መድረክም የአብሮነትን እሴት ለማዳበርና የሴቶችን አዎንታዊ አቅም ለማጎልብት እንዲቻል የመረጃ፣ የልምድ ልውውጥ የሚፈጥር መሆኑንና በቀጣይነትም የቅንጅታዊ ስራዎችን ለማጎልበት እንዲቻል የተሳበ መሆኑን አብራርተዋል፡፡
በእለቱም ክብርት ዶ/ር ኤርጎጌ ከአምባሳደር ኢቶ ታካኮ ጋር ሴቶችን መሰረት ያደረጉና በቅንጅት በሚሰሩ ስራዎች ላይ ሰፊ ውይይት አድርገዋል፡፡
Please follow and like us:

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *