የአረጋዊያንና የቤተሰብ ትስስር

አረጋዊያን በቤተሰብ ውስጥ ያላቸው ሚና አካላዊነቱ ይልቅ መንፈሳዊነቱ የጎላ ነው፡፡ በዚህ ዙሪያ ምርምር ያደረጉ ምሁራን Spiritual Head of the family ይሏቸዋል፡፡ ይህ ሁሉ በእድሜአቸው መቆጠር ሳይሆን ቤተሰብ በመንፈስ ተሳስሮና ጠንክሮ እንዲኖር ከሚያደርጉት ነገሮች መካከል ዋናዎቹ አረጋዊያን ለቤተሰብ አባላት የሚመግቧቸው የመንፈስ ምግቦች የተነሳ ነው፡፡

አረጋዊያን በቤተሰብ ውስጥ ህጻናትን በማነጽ፤ መልካም እሴቶችን በማስረጽ የሚጫወቱት ሚና በአስቸጋሪ የኑሮ ሁኔታዎች ውስጥ የቤተሰቡን አባላት በማረጋጋትና በመታደግ ደህንነት እንዲሰማቸው በማድረግ የሚጫወቱት ሚና በህብረተሰቡ ውስጥ ያላቸው ሚና እንዲገዝፍ አድርጎታል፡፡ በሌላ በኩል አረጋዊያን የአንድና ከአንድ በላይ ቤተሰቦች የተመሰረቱበት አምዶች ናቸው፡፡ በአንድ ቤተሰብ ውስጥ የአረጋዊያን መኖር ቤተሰቡን ምሉእ ያደርጋዋል፡፡

በአያቶቻቸው እየተመከሩና እየተገሩ ያደጉ ልጆች የህብረተሰቡን እሴት ተላብሰው የሚኖሩ ስብእናቸው በሚገባ የተገነባ ለሕብረተሰባቸውና ለአገራቸው የሚቆረቆሩ ናቸው፡፡ ዛሬ የምናያቸው አፈንጋጭ ባህሪያት (Deviation) በመልካም እሴቶች ተኮትኩቶ ካለማሳደግ የመነጩ መሆናቸውን አብዛኛው ሰው ይስማማበታል፡፡ ለዚህም መሰረታዊ ምክንያቱ የቤተሰብ የተቋጥሮ ዝምድና መላላት አንዱና ዋናው  ነው፡፡ የሚለው እሳቢ ትልቁን ስፍራ ይይዛል፡፡ ይህ ሲተነተን ለአረጋዊያን የምንሰጠው መንፈሳዊ ሚዛን ቦታውን እየለቀቀ መጣ ማለት ነው፡፡

እራሳቸውን እየዳበሱ ፀጉራቸውን እያሹ ተረትና ምሳሌ ይህን አርግ ይህን አታርግ እየተባሉ የሚታነጹ ህጻናት እምብዛም አለመገኘት የጎዳው በዋናነት ሕብረተሰብን እና ሀገርን ነው፡፡ የቤተሰብ ፍቅር የሌለው ዜጋ ለሕብረተሰቡም ለአገሩም ፍቅር የለውም ሚለው ድምዳሜ ላይ ያደርሰናል ማለት ነው፡፡ ወደ ማሰሪያው ስንመጣ በአሁኑ  የአረጋዊያን ለተለያዩ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ  ችግሮች የመጋለጥና አልፎ ተርፎም ደጋፊና ተንከባካቢ የማጣት ጉዳይ በላይ ሊያሳስበን የሚገባው አገር ተረካቢ ትውልድ የመፍጠር ጉዳይ ሊሆን ይገባል፡፡ ለዚህም አረጋዊያን በቤተሰብ ውስጥ ያላቸውን ሚና ማጠናከር የማህበረሰብ መልካም እሴቶችን መልስ የማጠናከር ስራ ተደርጎ ሊወሰድ ይገባል፡፡

Please follow and like us:

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *