በብሔራዊ የወጣቶች የዜግነት አገልግሎት ረቂቅ አዋጅ ላይ ውይይት ተካሄደ::

በብሔራዊ የወጣቶች የዜግነት አገልግሎት ረቂቅ አዋጅ ላይ ውይይት ተካሄደ::
***************
(ሐዋሳ – ጥር 3/2015 ዓም) የዜግነት አገልግሎት መስጠት እንዲያስችል በተዘጋጀ ረቂቅ አዋጅ ላይ ከሲዳማ ክልል ከተውጣጡ የቢሮ ኃላፊዎች፣ የወጣት አደረጃጀቶች፣ ወጣቶች እና ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ትካሄደ::
የሲዳማ ክልል የሴቶች፣ ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ ደስታ ለገሰ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር መንግስት የወጣቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚያስችሉ የተለያዩ ፖሊሲ ፣ የሕግና የአሰራር ማዕቀፎችን በማዘጋጀት በመተግበር እና በማስተግበር ላይ የሚገኝ ሲሆን በዚህም የክልሉ ወጣቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነትም እየጎለበተ መምጣቱን በመግለፅ አዋጁ መዘጋጀቱ የወጣቶችን ሳትፎ ይበልጥ እንደሚያጎለብትና የመድረኩ ተሳታፊ ወጣቶችም የክልሉ ወጣቶችን በመወከል ረቂቅ አዋጁን ለማዳበር የሚያስችሉ ጠቃሚ ግብአቶችን እንደሚሰጡ እምነታቸውን ገልፀዋል ::
በዕለቱ በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የወጣቶች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ማስፋፊያ ዴስክ ኃላፊ ሀብታሙ ከበደ በበሄራዊ አገልግሎት ፅንሰ ሃሳቦች እና ታሪካዊ ዳራ ዙሪያ ሰነድ ያቀረቡ ሲሆን የብሄራዊ የዜግነት አገልግሎት ረ ቂቅ አዋጅ ይዘት አስመልከቶ አቶ ገዳሙ ተሾመ በሚኒስቴር መ/ቤቱ የወጣቶች ብሄራዊ አገልግሎት ማስፋፊያ ደስክ ኃላፊ ባደረጉት ገለፃ የተለያዩ ሀገራት ተሞክሮ እንደሚያሳየው የወጣቶች ተሳትፎ ከሚጎለብትባቸው መንገዶች ውስጥ የዜግነት አገልግሎት አንዱ መሆኑን በመግለፅ ወጣቶች የእምቅ አቅም፣ ችሎታና ክህሎት ባልቤት እንደመሆናቸው ሀገርንና ራሳችውን በሚጠቅሙ ተግባራት ላይ በመሰምራት ለሀገረ መንግስት ግንባታ፣ ለማህበራዊ ደህንነት፣ ለሰላም መስፈን ወዘተ በፈቃደኛነት ላይ የተመሰረተ የዜግነት አገልግሎት በመስጠት ማህበራዊ ኋላፊነታቸውንና የዜግነት ግዴታቸውን መወጣት የሚችሉበትን ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር ታስቦ ረቂቅ አዋጁ መዘጋጀቱን ተናገረዋል::
በመጨረሻም በረቂቅ ሰነዱ ላይ ሰፊ ውይይት ከተደረገ በኃላ በተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ዙሪያ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቷል።
Please follow and like us:

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *