በበይነ መረብ አማካኝነት በህጻናት ላይ በሚፈጸሙ ወሲባዊ ጥቃቶች ዙሪያ የውይይት መድረክ ተካሄደ

በበይነ መረብ አማካኝነት በህጻናት ላይ በሚፈጸሙ ወሲባዊ ጥቃቶች ዙሪያ የውይይት መድረክ ተካሄደ
****************
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከዩኒሴፍ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር በበይነ መረብ የታገዙ በህጻናት ላይ የሚፈጸሙ ወሲባዊ ጥቃቶችን በተመለከተ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት የተሳተፉበት የውይይት መድረክ ጥር 2/2015 ዓ/ም በአዲስ አበባ ተካሂዷል፡፡
በውይይት መድረኩ በቀረበው የመነሻ ጽሁፍ በሀገራችን የተደረጉ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከአራት ህጻናት መካከል አንድ ህጻን የበይነ መረብ ተጠቃሚ እንደሆኑ ያሳያል፡፡ በተለይም ዕድሚያቸው ከ12-17 ክልል የሚገኙ ህጻናት የዲጅታል ቴክኖሎጅ/ኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ናቸው፡፡
በመሆኑም ህጻናት ኢንተርኔት ላይ በሚቆዩበት ጊዜ ከየትኛውም አይነት ጥቃት/በኢንተርኔት የታገዘ ወሲባዊ ጥቃትና ብዝበዛ እንዳይደርስባቸው የሚያስችል ዘርፈ ብዙ ስራዎች መሰራት እንዳለባቸው ተገልጿል፡፡
ሚ/ር መስርያቤቱ ከተለያዩ የመንግስት ተቋማት፣ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችን እና የኢንተርኔት አገልግሎት አቅራቢዎች/የቴክኖሎጂ ኢንዱስትሪ ጋር በጋራ በመሆን ህጻናት ኢንተርኔት በሚጠቀሙበት ወቅት ደህንነታቸው በተጠበቀ መልኩ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማስቻል ዘርፈ ብዙ ተግባራት መከናወን እንዳለባቸው በውይይቱ ተነስቷል፡፡
በሚ/ር መስርያቤቱ የህጻናት መብትና ጥበቃ ስራ አስፈጻሚ የጋራ ቴክኒካል አካል ለመቋቋም የተዘጋጀ መነሻ ሰነድ የቀረበ ሲሆን በተለይም በጥናቱ ግኝትና ምክረ ሀሳብ መሰረት የቴክኒክ ቡድን እንደ ሀገር ከህጻናት የኢንተርኔት አጠቃቀም ደህንንት ጋር በተያያዘ ያሉ አሰራሮችንና ስርዓት፣ ግንዛቤዎችን የማሳደገና ቴክኖሎጅዎችን በመፈተሽ የህጻናትን መብትና ደህንነት ለማስጠበቅ የሚያስችል ስራዎችን መስራት እንደሚያስፈልግ ተጠቁሟል፡፡
Please follow and like us:

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *