የአካል ጉዳተኞች የአካቶ ትግበራ ውይይት ተካሄደ፡፡

የአካል ጉዳተኞች የአካቶ ትግበራ ውይይት ተካሄደ፡፡
****************
(አዲስ አበባ፤ ጥር 5/2015) የእለቱን የመክፈቻ ንግግር የ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚ/ር የአካል ጉዳተኞች ጉዳይ ስራ አስፈፀሚ ተወካይ አቶ ሲሳይ ጥላሁን እንደገለፁት በሀገራችን የሚሰጡ በርካታ አገልግሎቶች የአካል ጉዳተኞችን ሁኔታ ግንዛቤ ውስጥ ያላካተቱ በመሆናቸዉ ሚ/ር መ/ቤቱ ይህንኑ ጉዳይ በመከታተል አካል ጉዳተኞችን ይበልጥ ተጠቃሚ የሚያደርጉ ስራዎች በመንግስትና መንግስታዊ ባልሆኑ ተቋማት ስራዎች እየተሰሩ ቢሆንም ጉዳዩ በሁሉም ተቋት ውስጥ ተካቶ እኩል ተጠቃሚነትን የማረጋገጥ ስራ ይቀራል ብለዋል፡፡
አክለውም ሚ/ር መ/ቤቱ አካል ጉዳተኞችን የተመለከቱ የህግ ማዕቀፎች እንዲዘጋጁና እንዲተገበሩ ከማድረግ ባሻገር ተፈጻሚነታቸዉን ከሚመለከታቸዉ አካላት ጋር በመሆን የመከታተል ስራ በመስራት ላይ የሚገኝ በመሆኑ ህጎችን በመተግበር ደረጃ የአካቶ ትግበራ ስራ ዋና በመሆኑ የተለያዩ ተቋማት ያላቸውን ልምድ ለመለዋወጥና በቀጣይ የመፍትሄ ሀሳቦች ለማመላከት ይህ የመድረክ ውይይት አስፈልጓል ብለዋል ፡፡
ኤርምያ መኮንን የቼሻየር ኢትዮጵያ ፕሮግራም ዳይሬክተር ፅሁፍ ያቀረቡ ሲሆን በፅሁፋቸውም የአካል ጉዳተኞች አጠቃላይ ትርጉም ፤የአንድ አገር ሁለንተናዊ እድገት የሚባለው ሁሉን አቀፍ የሆነ የኢኮኖሚያዊ፤ማህበራዊ እና ፖለካዊ እድገት ሲኖር በመሆኑ አካል ጉዳተኞች የአገሪቱ ልማት ተጠቃሚ ከመሆን አንፃር በርካታ ስራዎች እንደሚቀሩና አካል ጉዳተኞችንና ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎችን ያላገናአበ ልማት ቀጣይነት የሌው ልማት ወይም እድገት ይሆናል ብለዋል፡፡ላይ የሚሰሩ፡፡ በመሆኑም ማንኛውም ተቋም በሚያከናውነው ተግበር ውስጥ አካል ጉዳተኞችን ያገናዘበና ያሳተፈ መሆን አለበት ብለዋል፡፡ በቀረባ ፅሁፍ የተለያዩ ተቋማት በምን ሁኔታ ማካተትን እንደሚተገብሩ በምሳሌነት በመጥቀስ አብራርተዋል፡፡
የሚ/ር መ/ቤቱ የአካል ጉዳተኞች ከፍተኛ ባለሞያ አቶ ማህሙድ ከድር ተተቋማት በምን መልኩ የአካል ጉዳተኞችን ጉዳይ የማካተትና ተጠቃሚነትን የማረጋገጥ ተግባር መስራት እንዳለባቸው ባቀረቡት ፅሁፋቸው ገልፀዋል።
በመጨረሻም ከአካል ጉዳተኞች ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን በቡድን ውይይት ተደርጎ አጠቃላይ አቅጣጫ ተሰጥቶበት ውይይቱ ተጠናቋል ።
Please follow and like us:

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *