የህጻናት ማዋያ ተቋማትን ለማጠናከር የግሉ ዘርፍ የሚያደርገውን ተሳትፎ ማጎልበት ተገቢ እንደሆነ ተገለፀ፡፡

የህጻናት ማዋያ ተቋማትን ለማጠናከር የግሉ ዘርፍ የሚያደርገውን ተሳትፎ ማጎልበት ተገቢ እንደሆነ ተገለፀ፡፡
**************************
(አዲስ አበባ፣ ጥር 14/2015 ዓ.ም) የኪንደር ህፃናት ማቆያ(Kinder daycare) ዛሬ ጥር 14 ቀን 2015 ዓ.ም በጀሞ አካባቢ የአገልግሎት አሰጣቱን ለማስተዋወቅ የጉብኝት ፕሮገራም አካሄደ፡፡
ፕሮግራሞን በንግግር ያስጀመሩት የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የሴቶችና ህፃናት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አለሚቱ ኦሞድ እንደገለፁት የአንድ አገር መሰረት ሰው መሆኑን ገልፀው ሰው ደግሞ ሙሉ ስብዕና ኖረት አገርን ሊጠቅም የሚችልበት ደረጃ ከህፃንነት ጀምሮ በየደረጃው የትውልድ ስብዕና ግንባታን በመንግስትና በግሉ ዘርፍ አጠናክሮ ሲሰራ ነው ብለዋል፡፡
ክብርት ሚኒስትሯ አክለውም የኪንደር ደይኬር ባለቤት ወ/ሮ ሳራና ባለቤትዋ አቶ ቶማስ ይህን ስራ መጀመራቸው በርካታ ወላጆች ያለስጋት ልጆቻቸውን በማቆያው አስረክበው ተረጋግተው ስራቸውን እንዲሰሩ ከመርዳት ባሻገር ለሌሎች ዜጎች የስራ እድል መፍጠርና የማህበራዊ ችግሮችን በማቃለል እጅግ ከፍተኛ ጠቀሚታ አለው ብለዋል፡፡ በመሆኑም ምንም እንኳ መንግስት በዚህ ዘርፍ በመንግስት ተቋማት ውስጥ የህፃናት ማቆያ በመሰራት ጥረት እያደረገ ቢገኝም ከስራው ስፋት የተነሳ የግሉ ባለሀብት መሳተፍ እንዳለበት በመጠቆም ሚኒስቴር መ/ቤቱም በዚህ ዘርፍ ለመሰማራት ፍላጎት ያላቸውን ባለሀብቶች አሰፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ ገልፀው በዚህ አጋጣሚ የኪንደር ደይኬር ባለቤት በሚ/ር መ/ቤቱ ስም በማመስገን ይህንን ልምድ ለሌሎች በማካፈል በጋራ የአገራችንን ማህበራዊ ችግሮች መቅረፍ ይገባናል ብለዋል፡፡
የኪንደር ደይኬር ባለቤት ወ/ሮ ሳራ ወደዚህ ስራ ያስገባቸው ዋናው ምክንያት እራሳቸው ተጠቃሚ ስለነበሩ ችግሩ ምን ያህል የገዘፈና ትኩረት ያልተሰጠው በመሆኑ ነው የጀመርኩት ብለዋል፡፡
Please follow and like us:

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *