በጦርነት ምክንያት የተፈናቀሉና ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች ጊዜያዊ ማገገሚያ ማዕከል ተመረቀ

(ጥር 18/2015 አፋር፤ሰመራ) በአፋር ክልል በሰመራ ከተማ ተገንብቶ አገልግሎት ሲሰጥ የነበረው የተሃድሶ ማዕከል በመንግስት በጀት እድሳት ተደርጎለት በዛሬው እለት ከፍተኛ የመንግስት አካላት በተገኙበት ተመረቀ፡፡ በምርቃት ስነስረዓቱ ላይ የተገኙት የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የሴቶችና ህጻናት ዘርፍ ሚኒሰትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አለሚቱ ኡመድ እንደገለፁት ይህን በአገር ላይ የተፈጠረውን አደጋ ለመቅረፍ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ግለሰቦችና ባለሀብቶች በጋራ በመስራት መፍትሄ ማምጣት ተገቢ ጉዳይ ነው ብለዋል፡፡ ሚኒስትሯ አክለውም ይህ የምንገኝበት መአከል በጦርነቱ ምክንያት የተፈናቀሉ ዜጎች በጊዜዊ ማረፍያነት አገልግሎት በሚሰጥበት ወቅት ጉዳት የደረሱበትን በመንግስት በተደረገ የበጅት ድጎማ አድሳት የተደረገለት የተሃድሶ ማእከል ነው ብለዋል፡፡
በመርሃ ግብሩ የክልሉ የሴተቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ አይሻ ያሲን እንደገለፁት ማዕከሉ ቀደም ብሎ ለምረቃ ዝግጅት በሚደረግበት ወቅተ ጦርነቱ በመከሰቱ ማእከሉ ከትግራይ ለመጡ ወንድሞችና እህቶች ማረፊያ ሆኖ ሲያገለግል መቆየቱንና በታቀደው መንገድ አገልግሎት መስጠት ሳይችል ቆይቶ ነበር ብለዋል፡፡ ሆኖም ግን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ባደረገው ድጋፍ አድሳት ተደርጎለት ለአገልግሎት እንዲበቃ በመደረጉ ለሚኒስቴር መ/ቤቱ ምስጋናቸውን በማቅረብ አጋር አካላት በቀጣይም ማዕከሉን የማገዝና የመደገፍ ስራ እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡በእለቱ በተደረገው የምክክር መድረክ በጦርነቱ በተጎዱ አካባቢዎች የደረሱ አጠቃላይ ጉዳቶችን በተመለከተ የዳሰሳ ጥናት የቀረበ ሲሆን በጥናቱም ግጭት በደረሰባቸው አከባቢዎች የደረሱ ጉዳቶችን በተለይም ጉዳት የደረሰባቸውን ሴቶች በመደገፍ የተሰሩ ስራዎች፤ ያጋጠሙ ተግዳሮቶች እና በቀጣይ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስፈልጉ ድጋፎች ቀርበዋል፡፡
በቀጣይ ማዕከሉ ያልተሟሉለትን ግብዓቶች በማሟላትና በማጠናከር ተገቢውን አገልግሎት እንዲሰጥ በማድረግ ረገድ ስራውን በማስተባበር ሚና ሊወጣ የሚችል ጠንካራ ጥምረትና የጋራ እቅድ አውጥቶ መተግበር እንዳለበት በመድረኩ ተግልጧል፡፡ በዛሬው እለት የተመረቀው ተቋም ወደ ስራ እንዲገባ በተለይም በሴቶች ላይ በሚደርሱ ጥቃቶች መከላከልና ምላሽ የመስጠት ፕሮግራም ላይ የሚሰሩ አጋር አካላትን ያሳተፈ የቴክኒክ ኮሚቴ ማቋቋምና የተቀናጀ እቅድ መዘጋጀት እንዳለበት እንደየተቋማቸው የስራ ባህሪ (Comparative Advantage) መንግስት እየወሰደ ያለውን ከፍተኛ ድርሻ መደገፍ እንዳለባቸው ፣ የድጋፍና የአገልግሎት አሰጣጡ ስረዓት መዘርጋት እንዳለበት፣ የስራ ድግግሞሽ በሚየስቀር መልኩ በቅንጅት መስራት እንደሚጠበቅባቸውና ለመደገፍ ዝግጁ መሆናቸውን በመግለፅ የጋራ ስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡
በማጠቃለያ ክብርት ወ/ሮ አለሚቱ ኡመድ የደረሱት ጉዳቶችና እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ተመጣጣኝ እንዳልሆኑ ጠቁመው በቀጣይ ሁሉም አጋር አካላት በመቀናጀት የጋራ ርብርቦሽ እንደሚያሰፈልግና የዜግነት ግዴታን መወጣት ከምንግዜውም በላይ አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡ከመርሀ ግብሩ ጎን ለጎን የችግኝ ተከላና የጉብኝት ስነስረዓት ተካሄዷል፡፡
Please follow and like us:

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *