በቤተሰብ መልካም እሴቶች አጠባበቅ ዙርያ ለሚዲያ ተቋማት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ

(ጥር 26/2015 ዓ.ም አዳማ) ከፌዴራል የመንግስትና የግል ሚዲያ ተቋማትና ክልልና ከተማ አስተዳደር የህዝብ ግንኙነትና ኮሚኒኬሽን ቢሮ ባለሞያዎች በቤተሰብ መልካም እሴቶች አጠባበቅ ዙርያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መርሀ-ግብር ተካሄደ፡፡
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የአረጋዊያን እና ቤተሰብ ጉዳይ መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ ተስፋዬ ሮበሌ በመክፈቻ ንግግራቸው እንደገለፁት ቤተሰብ የህብረተሰብ ሶሻል ዩኒቲ በመሆኑ ሁሉም ማንበረሰብና የሀገር መሰረት ነው ተብለዋል ።ማንኛውም ግለሰብ፣ ማህበረሰብ እና ሀገር ከቤተሰብ ውጪ የተገኘ አለመሆኑን አንስተዋል፡፡
ቤተሰብ ለመልካምም ሆነ መጥፎ ነገሮች ለመፍጠር መነሻ ሊሆን ይችላል፤ስለ ቤተሰብ እሴቶችን አበክረን በጋራ ካልሰራንበት እየተሸረሸሩና እየጠፉ ያሉ እሴቶች የአገርን ህልውና አደጋ ላይ ሊጥሉ ይችላሉ ብለዋል።
አክለውም የቤተሰብ ምስረታም ከተቃራኒ ፆታ ወጥቶ ወደ ተመሳሳይ ፆታ የሚጋቡበት አለም ላይ መድረሱን አንስተው ይህ መድረክም በተለይ የሚዲያ ተቋማትና ሚዲያዎችን የምትመሩ ኃላፊዎች ስለቤተሰብ እንደመንግስትም ሆነ እንደሚኒስቴር መስሪያ ቤታችን በሁን ጊዜ ለቤተሰብ የተሰጠውን ትኩረት አውቃችሁ ግንዛቤ፣ እንዲኖርአችሁና የራሳችውን ድርሻ መወጣት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል ተብለዋል።
የመገናኛ ብዙሃን አዋጅ ቁጥር 1238/2013 የሕዝብ የብሮድካስት አገልግሎቶችን ጨምሮ ሌሎች የአገልግሎት አይነቶች በአንቀጽ 55/1/ሐ ላይ እንደተገለጸው ‹ለአገሪቱ ፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ዕድገትና ብልፅግና፣ እንዲሁም በህገ መንግስቱና በሌሎች የህዝብ ጥቅምና የጋራ አገራዊ እሴቶች እንዲጠናከሩ አስተዋጽኦ የሚያደርግ የብሮድካስት አገልግሎት የመስጠት›ግዴታ እንዳለባቸው በግልጽ ይደነግጋል፡፡ እንዲሁም በዚሁ አንቀጽ መ. ላይ ‹የማህበረሰቡን ባህላዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ መሠረቶች የሚጠብቁ፣ የሚያጠናክሩና የሚያሳድጉ ፕሮግራሞችን የማቅረብ ግዴታም እንዳለባቸው ተመላክቷል፡፡
የመድረኩን አስፈላጊነት በፅሁፋቸው ያቀረቡት አቶ ዋሲሁን እንደገለፁት ዋናው አላማም የቤተሰብ መልካም እሴቶች በተለይ በመገናኛ ብዙሃን በሚሰራጩ አሉታዊ የፕሮግራም አቀራረቦች እና መልእክቶች ምክንያት ጉዳት እንዳይደርስባቸው ለመከላከል፣ የቤተሰብ ጉዳይ እንደ ሀገር ወሳኝ መሰረታዊ ጉዳይ ስለሆነ የሚድያ ተቋማት ይህንኑ በአግባቡ ተረድተው ትኩረት እንዲሰጡት ለማስቻል፣ ቤተሰብን የተመለከቱ ፕሮግራሞች ሲሰራጩ ሊጠበቁ የሚገባቸውን እሴቶች ለማስተዋወቅ፣ የሚተላለፉ ቃላቶችን፤ ምስሎችና መልእክቶችን ጤናማ እንዲሆኑ ለማስቻል፣ ስለቤተሰብ በዕቅድ ይዘው መደበኛ ፕሮግራሞችን የሚያሰራጩበትን ሁኔታ ለማመቻቸት እንዲረዳ ስልጠናው አስፈላጊ በመሆኑ ነው ተብለዋል ፡፡
በመርሀ-ግብሩም የቤተሰብ ጉዳዮችን በተመለከተ ትኩረት የተሰጣቸው ዋና ዋና ጉዳዮች፣ የቤተሰብ ተፈጥሯዊ አወቃቀር የሚሰጡ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ምክንያቶች እና የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም ችግሮች በተመለከተ ጹሁፍ ቀርቦ ሰፊ ውይይት በማድረግ ለቀጣይ ስራዎች ግብዓት የሚሆኑ አስተያየቶችም ከተሳታፊዎች ማግኘት ተችሏል፡፡
በተጨማሪምየጋብቻ እና ቤተሰብ አማካሪ ሆኑት አቶ ይመስገን ሞላ የቤተሰብ ጉዳዮች የሚዲያ ፕሮግራም ዝግጅትና ዘገባ ጥንቃቄዎች ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥተዋል፡፡
በመጨረሻም የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አቶ ተስፋዬ ሮበሌ በማጠቃለያው ንግግራቸው የቤተሰብ ጉዳይ አንዴ ተነስቶ የሚቆም ሳይሆን ቀጣይነት ያለው ሂደት ነው፤ በቀጣይም እንደ ሀገር የቤተሰብን ቀን ለማክበር በዝግጅት ላይ እንገኛለን እናንተም እንደሚዲያ ለዚህ ዝግጅት እንድት ዘጋጁና ትኩረት ሰጥታችው እንድሰሩ አደራ ማለት እወዳለው በማለት በርሀ-ግብሩ ተጠናቋል፡፡
Please follow and like us:

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *