የአንድ አገልግሎት ማዕከል መስጫ ማዕከል ግንባታ በሶማሌ ክልላዊ መንግስት በጎዴ ከተማ ተመረቀ::

በሴቶችና ህጻናት ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን ተገቢውን ምላሽ እና እንክብካቤ ለመስጠት የሚያግዝ ማእከል ለመገንባት የሴቶችናማ ሕበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አለሚቱ ዑመድ ከሶማሌ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ርእሰመስተዳደር ምክትልኃላፊ፤ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ፤ የዩኒሴፍ ከፍተኛ አመራሮች እና በኢትዮጵያ የጀርመን አምባሳደርና ምክትል አምባሳደር በተገኙበት በጎዴ ከተማ በሴቶችናህ ጻናት ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን ምላሽለ መስጠት እና ለመከላከል የሚያግዝ ማዕከል ግንባታ ተመረቀ፡፡

ክብርት ሚኒስትር ዴኤታዎ በምረቃ ስነስረዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር ማዕከሉ በሀገራችን የሚደርስ ጥቃት እንዲቆም፣ ጥቃት የደረሰባቸው ሴቶችና ህፃናት ተገቢውን ህክምና እና ፍትህ እንዲ ያገኙ ጥበቃና ከለላ እንዲደረግላቸው፣ የስነ ልቦና ድጋፍ እንዲደረጉ በጥቅሉ ጥቃት የደረሰባቸው ሴቶችና ህፃናት ተገቢውን ምላሽ በመስጠት በሁሉም ደረጃ የሚገኙ አደረጃጀቶች እና ድርጅቶች ርብርብ ይጠይቃል ብለዋል።

ክብርት ሚኒስሯ አያይዘውም ማዕከሉን ለመገንባትና በዚህ ደረጃ እውን እነዲሆን የገንዘብ ድጋፍ ላደረጉት የዩኒሴፍና የጀርመን ኤምባሴም በሚኒስቴር መስርያቤቱ እና በኤትዮጵያ መንግስት ስም ከፍ ለ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

በምርቃት ስነስረዓቱ ላይ ልዩልዩ ተቋማትን የወከሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በማዕከሉ መገንባት ከፍ ያለ ደስታ እንደተሰማቸውና በቀጣይ በሴቶችና ህፃናት ዙርያ ለሚሰሩ ስራዎች መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት በቅንጅት መስራት እንዳለባቸው ገልፀዋል፡፡

ከተያዘው መርሃ ግብር በተጨማሪ በክልሉ በተከሰተው ድርቅ ምክንያት ተፈናቅለው በአንድ አካባቢ እየተረዱ ያሉ ዜግችንንም የመጎብኘት ስነ ስረዓት ተካሄድዋል፡፡በጉብኝቱ ምህፃናት ትምህርት እንዲያገኙ የትምህርቤት ግንባታ እና ሌሎች ቆሳቁሶች እየተሟሉ መሆኑንና በቀጣይ በአካባቢው ያለውን ከፍተኛ የውሃ ችግር ለመቅረፍ የዩኒሴፍና የጀርመን ኤምባሲ ጥረት እንደሚደርጉ በጉብኝቱ ስነስረዓት ገልፀዋል፡፡

 

 

Please follow and like us:

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *