የኢትዮጵያ ወጣቶች ምክር ቤት ለማቋቋም በተዘጋጀ መነሻ ሰነድና የአደረጃጀት ደንብ ላይ ውይይት ተካሄደ

(አዲስ አበባ፣ መጋቢት 22/2015 ዓ.ም) የኢትዮጵያ ወጣቶች ም/ቤት ለወጣቶች ድምፅ! እና የወጣቶች ንቁ ተሳትፎ ለኢትዮጵ ከፍታ! በሚል መሪ ቃል መጋቢት 24 ቀን 2024 ዓ.ም በደማቅ ሰነ ስረዓት የሚከበረውን የኢትዮጵያ ወጣቶች ም/ቤት ምስረታ ምክንያት በማድረግ ከፍተኛ ቅድመ ዝግጅት እየተካደ ይገኛል፡፡

የቅድመ ዝግጅቱ አካል የሆነው አንዱ ፕሮግራም ዛሬ መጋቢት 22 ቀን 2024 ዓ.ም በእስካይ ላይት ሆቴል የኢትዮጵያ ወጣቶች ምክር ቤት ለማቋቋም በተዘጋጀ መነሻ ሰነድና የአደረጃጀት ደንብ ላይ ውይይት እየተካሄደ ይገኛል፡፡

በመርሀ ግብሩ ላይ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የወጣቶች ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ ሙና አህመድ በመክፈቻ ንግግራቸው ሰነዶቹ በተለያዩ ጊዜያት ሲዳብሩ የመጡ መሆኑን ጠቁመው በህገ−መንግስት የመደራጀት መብት መሰረት ነፃ አደረጃጀት፣ ሁሉንም አቃፊ የሆነ፣ የተመሰረተበትን አላማ የሚያሳካ፣ በወጣት ዘንድ ለመደራጀት ተነሳሽነትን የሚፈጥር፣ ለወጣት ድምጽ የሚሆን፣ ከመንግስት ጋር በወጣቶች ጉዳይ የሚመክር፣ ጊዜውን የዋጀ ከፌዴራል ጀምሮ በተዋረድ እስከ ክልል ድረስ ተመሳሳይ መዋቅር ያለው አደረጃጀት እንዲፈጠር ነው ብለዋል። በዚህ ረገድ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴ የኢትዮጵያ ወጣት ምክር ቤት ጠንካራ፤ አካታችና አሳታፊ የሆነ አደረጃጀት እንዲኖር የሚጠበቅበትን ተግባር ሁሉ እንደሚያከናውን ለመድረኩ ገልፀዋል፡፡

Please follow and like us:

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *