የኢትዮጵያ ወጣቶች ምክር ቤት የሚመሩ ፕሬዝደንትና ስራ አስፈፃሚዎች ምርጫ ተካሄደ

(አዲስ አበባ፣ መጋቢት 23/ 2015) በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚቋቋመውን የኢትዮጵያ ወጣቶች ምክር ቤት የሚመሩ አካላት ምርጫ ተካሄደ ውጤቱም በነገው የም/ቤት ምስረታ ላይ እንደሚገለፅ ተጠቆመ።

‘የኢትዮጵያ ወጣቶች ምክር ቤት ለወጣቶች ድምፅ’ በሚል መሪ ቃል በዛሬው ዕለት እየተካሄደ ባለው የምርጫ ሂደት ከትግራይ በስተቀር ከሁሉም ክልሎች እና ከሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ ወጣቶች እየተሳተፉ ይገኛሉ።

በመድረኩ ላይ ሚኒስትሯ ክብርትት ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ እንደናገሩት፤ ወጣቶች ካላቸው እምቅ አቅም፣ እውቀትና ክህሎት አንፃር ለሀገር ዕድገትና ብልፅግና የሚያበረክቱት አስተዋፅዖ ከፍተኛ በመሆኑ መንግስት የወጣቶችን ችግሮች ለመፍታት፣ መብታቸውንና ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

ህገመንግስቱንና ፖሊሲውን መሠረት በማድረግ በርካታ የወጣት አደረጃጀቶች ተቋቁመው የተለያዩ ተግባራትን ሲያከናውኑ መቆየታቸውን አንስተዋል።

ሆኖም አደረጃጀቶቹ በመንግስትና በሀገራችን ወጣቶች መካከል ድልድይ ሆኖ የሚያገለግል፣ በወጣቶች የሚመራና ከመንግስት ጋር በመካከር የሚሰራ፣ እውነተኛ ድምፅ የሚሆንና ኢትዮጵያን የሚመስል ጠንካራ አደረጃጀት መፍጠር አስፈላጊ ሆኖ መገኘቱን ጠቁመዋል።

በመሆኑም ሚኒስቴር መ/ቤቱ ከወጣት አደረጃጀቶች ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት ሲሰራ መቆየቱን ተናግረዋል።

በአሁኑ ወቅትም ሁሉንም የወጣት ህብረተሰብ ክፍል ሊወክል የሚችል ሀገር አቀፍ የወጣቶች ምክር ቤት ለማቋቋም ዝግጅቱ መጠናቀቁን ገልፀዋል።

በዚህ መነሻነት ከትናንት መጋቢት 22 ጀምሮ ምክር ቤቱ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ሲወያይ ቆይቷል፤ በዛሬው ዕለትም የሚመሩ አባላት ምክር ቤቱን በቀጣዮቹ ጊዜያት የሚመሩ ፕሬዝደንትና ስራ አስፈፃሚ አካላትን ምርጫ አካሂዷል።

Please follow and like us:

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *