በሳውዲ አረቢያ በችግር ውስጥ የነበሩ ከመቶ ሰላሳ ሺህ በላይ ዜጎች ወደሀገር እንዲመለሱ ማድረግ ተችሏል።

ከመጋቢት 21 ቀን 2014 ዓ.ም እስከ መጋቢት 25 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ በተሰራ ስራ በሳውዲ አረቢያ በችግር ውስጥ የነበሩ 133,103 ዜጎችን ወደ ሀገር መመለስ ተችሏል።

ወደ ሀገር ከተመለሱት 133,103 ዜጎች መካከል 110,587 ወንዶች፣ 15,799 ሴቶች እና 6,717 ህፃናትና እድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ናቸው።

ለተመላሽ ዜጎች ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ስራ ተሰርቷል፡፡

መንግስት በመጀመሪያ ዙር በሳውዲ አረቢያ በችግር ውስጥ የነበሩ 102 ሺህ ዜጎችን ወደ ሀገር ለመመለስ ማቀዱ የሚታወስ ነው።

Please follow and like us:

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *