ከእኛ ጋር ለእኛ እንስራ

ከእኛ ጋር ለእኛ እንስራ

ዓለማየሁ ማሞ (ከአ/ጉ/ ጉ መሪ ስራ አስፈጻሚ)
የአእምሮ እድገት ውሱንነት (Down Sybndrome) ማለት – የአእምሮ ብስለት ጉልህ በሆነ ልዩነት ከአማካዩ በታች
መሆንና የግላዊና ማህበራዊ ክንዋኔዎች ብቃት መጓደል ማለት ነው:: የአእምሮ እድገት ውሱንነት ያለባቸው ህጻናትና
ወጣቶች በአእምሮአዋ እድገታቸው በስሜት ህዋሳታቸው መዳበርና በማህበራዊ ግንኙነቶች ከእድሜ እኩዮቻቸው አንጻር
ውሱንነት የሚታይባቸው ናቸው፡፡
የአእምሮ እድገት ውሱንነት አንድና ከአንድ በላይ በእለት ከዕለት የሚከናወኑ ተግባራትና ባህርያት የሚገለጽ ሲሆን
እነእርሱም የመግባባት ፣ ራስን የመንከባከብ ፣ የአኗኗር የማህበራዊ ክህሎቶች ፣ የንብረት አጠቃቀም ፣ ራስን
የመምራት ፣ ለራስ የሚደረግ ጥንቃቄ ፣ የቀለም ትምህርቶችን የመማር ውሱንነቶች ሲሆኑ መገለጫቸውም በመኖሪያ
ቤት ፣ በትምህርት ቤት፣ በመዝናኛና በስራ ቦታ በሌሎች ማህበራዊ መስተጋብሮች በሚከናወኑባቸው ስፍራዎች የሚታይ
ውሱንነት ነው፡፡
በተለምዶ አንድ ሕፃን 46 ክሮሞዞሞችን ይዞ ይወለዳል፡፡ ዳውን ሲንድሮም ያለባቸው ሕፃናት ከእነዚህ ክሮሞዞሞች
በተጨማሪ 21 ቅጂ አላቸው። የክሮሞዞም ተጨማሪ ቅጂ በሕክምና አጠራር ቃል ‘trisomy’ ነው። ዳውን
ሲንድሮም ደግሞ ትራይሶሚ 21 ተብሎ ይጠራል።
ይህ ተጨማሪ ቅጂ የሕፃኑ አካል እና አንጎል እድገት ላይ ተጽዕኖ ያለው ሲሆን በህፃኑ አእምሮአዊ እና አካላዊ እድገት ላይ
ውሱንነትን ሊያስከትል ይችላል፡፡ ዳውን ሲንድሮም ያለባቸው ሰዎች ተመሳሳይ ቢመስሉም እያንዳንዱ ሰው የተለያየ
ችሎታ አለው፡፡
በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በየዓመቱ ወደ 6,000 የሚጠጉ ሕፃናት ዳውን ሲንድሮም ክስተት ጋር የሚወለዱ ሲሆን ይህ
ማለት ከ 700 ሕፃናት ውስጥ በአንድ ህጻን ላይ ዳውን ሲንድሮም ውስጥ ይከሰታል ማለት ነው፡፡
ይህ የሚያሳየን ዳውን ሲንድረም ያለባቸው ህጻናት በሃገራችን ኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በሁሉም የዓለማችን ክፍሎች
የሚገኙ መሆኑን በመገንዘብ የህጻናቱን ዘላቂ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ለመፍትሔው በጋራ መረባረብ እንደሚገባ
የሚያስገነዝብ ነው፡፡
ከተለመዱት የዳውን ሲንድረም አካላዊ ገጽታዎች መካከል የጡንቻ ዝቅተኝነት ፣ አጠር ያለ ቁመት ፣ ወደ ላይ ሰቀል
ያለ አይንና ዝቅ ያሉ ጆሮዎች ጥቂቶቹ ናቸው፡፡
የአእምሮ እድገት ውሱንነትን ያለባቸው ዜጎች ቁጥር ከሚያበራክቱና በማህበረሰቡ ውስጥ በሚገኙ ግለሰቦች
ከሚፈጠሩ ሰው ሰራሽ ምክንያቶች መካከል የቤተሰብ መፍረስ፣ የወላጆች ወይም የአሳዳጊዎች ቸልተኝነት ፣ የአልኮል
ሱሰኝነት፣ ያለ ሃኪም ትዕዛዝ የሚወሰዱ መድሃኒቶችና አደንዛዥ ዕጾች፣ ተጠቃሾች ናቸው፤፡
እነዚህን ሰው ሰራሽ ምክንያቶች ህብረተሰቡ ለመቆጣጠር፣ ለመከላከልና ለማስወገድ ቢችል በየዕለቱ እየጨመረ
የሚሄደውን የአእምሮ እድገት ውሱንነትን ያለባቸው ዜጎች ቁጥር ለመቀነስ ከፍተኛ አስተዋጽዖ እንዳለው ለመረዳት
አያዳግትም፡፡

የአእምሮ እድገት ውሱንነትን መከላከል የሚቻለው የችግሩ መንስኤ የሆኑትን ነገሮች በመለየት ችግሩ እንዳይከሰት
ተከስቶ ሲገኝ ደግሞ በወቅቱ ለተከሰተው ችግር መፍትሔ በማፈላለግና እንደ ጉዳቱ አይነት ተገቢ የሆነውን እገዛ ማድረግ
ያስፈልጋል፡፡
እነዚህን የመፍትሔ ሃሳቦችና ወቅታዊ ድጋፎችን ለሁሉም እኩል ተደራሽ ተጠቃሽ የህግ ማዕቀፎች አንዱ የተባበሩት
መንግስታት ሰብዓዊ መብቶች የአካል ጉዳተኞች መብቶች ኮንቬንሽን ተጠቃሽ ነው፡፡
ኮንቬንሽኙን መሰረት በማድረግ መከበር የጀመረው ዓለም አቀፍ የዳውን ሲንድሮም ቀን በተባበሩት መንግስታት ጠቅላላ
ጉባኤ በየዓመቱ መጋቢት 12 ቀን / /እ.ኤ.አ. ማርች 21 ቀን 2012 / ቀን እንዲከበር በመወሰኑ ነው፤፡፡
ውሳኔው ሁሉም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አባል ሀገራት፣ አለም አቀፍ ድርጅቶች መንግሥታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ
ተቋማት ጉዳዩን በባለቤትነት እንዲያስፈጽሙት ጥሪ የሚያቀርብ ነው፡፡
በዚህ መሰረት የዓለም አቀፍ የዳውን ሲንድሮም ቀን በአለም አቀፍ ደረጃ ለ12ኛ በሃገራችን ደግሞ ለ8ኛ ጊዜ "ከእኛ
ጋር ለእኛ እንስራ!" በሚል መሪ ቃል በመከበር ላይ ይገኛል ፡፡
በዓሉ ይህን የያዝነውን የመጋቢት ወር ቀናት በመጠቀም ህብረተሰቡን ግንዛቤ የሚያስጨብጡ የተለያዩ ትምህርታዊ
ይዘት ያላቸው ተግባራት የሚከናወንበት ሲሆን ሁሉም የመገናኛ ብዙሃን የአእምሮ እድገት ውሱንነትን እንደ አንድ
ወቅታዊ ጉዳይ አጀንዳቸው በማድረግ ህብረተሰቡን ግንዛቤ የሚያስጨብጡበት ይሆናል፡፡
"ከእኛ ጋር ለእኛ እንስራ! የሚለውን መሪ ቃል መሰረት በማድረግ የሚከበረው አለም አቀፍ የዳውን ሲንድረም ቀን
ዋና ዓላማ ን የበዓሉን ባለቤቶች ከህብረተሰቡ ጋር በማስተዋወቅና ተሳትፎዋቸውን በሚያጎልብቱ ፣ በሁሉም ዘርፍ
በሚያካትቱና ተጠቃሚ በሚያደርጉ መርሃ ግብሮች ባለቤት በማድረግ ስለራሳቸው ራሳቸው እንዲናገሩና ለአካል ጉዳተኞች
እኩል መብቶች መከበር ቁልፍ የሆነውን የሰብዓዊ መብቶች እይታ ጥብቅና እንዲቆሙ ከማበረታታት በተጓዳኝ ዳውን
ሲንድረም ያለባቸው ዜጎችን የሚመለከቱ ትክክለኛና ወቅታዊ መረጃዎችን ለህብረተሰቡ ተደራሽ በማድረግ የበኩላቸውን
አስተዋጽዖ እንዲያበረክቱ ምቹ ሁኔታዎችን የሚፈጥር ነው፡፡
በዚህ መሰረት የአእምሮ እድገት ውሱንነት ካለባቸው ዜጎችና ከወላጆቻቸው ጋር በቅንጅት በመስራት እነዚህ ሕጻናት
በልጅነት ሲገኙ ወደ ትምህርት ቤት በማስገባት፣ ወጣቶችን በተለያዩ ሙያዊ ስልጠናዎች በማሳተፍና በኢኮኖሚ
ራሳቸውን እንዲችሉ በማድረግ እንዲሁም ወላጆቻቸውን በኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራሞች ተጠቃሚ በማድረግ የጎላ
አስተዋጽዖ በማድረግ ላይ ለሚገኘው ፍቅር የኢትዮጵያ የአእምሮ እድገት ውሱንነት ብሔራዊ ማህበር ትልቅ አክብሮት
ያለን መሆኑን እየገለጽን ማህበሩ በሚሰጣቸው አገልግሎቶች ያለንን አድናቆት ተጠቃሚ በሆኑ ህጻናትና በሚኒስቴር
መስሪያ ቤቱ ስም ልባዊ ምስጋናችንን ለማቅረብ እንወዳለን፡፡
በያዝነው የመጋቢት ወር ለአእምሮ እድገት ውሱንነት የሚታይባቸው ዜጎቻችን እንክብካቤና ድጋፍ በሚያገኙባቸው
ተቋማት በመገኘት አብሮነታችንን በተግባር በማሳየት ፣ የበጎ ፍቃድ አገልግሎት በመስጠትና አስፈላጊውን የፋይናንስ
የቁሳቁስና የሃሳብ ድጋፍና አስተዋጽዖ ማድረግ እንዲሁም ከፍቅር የኢትዮጵያ የአእምሮ እድገት ውሱንነት ብሔራዊ
ማህበር ጋር በቅንጅት ለመስራት የሁላችንንም ርብርብ የሚጠይቅ ነው፡፡
በዘላቂነትም ለአካል ጉዳተኞችን መብቶች በማክበርና በማስከበር፣ የመደጋገፍ ባህላችን የሚጎለብትበት ፣ በሃላፊነት፣
በቁርጠኝነትና በባለቤትነት በመስራት የአካል ጉዳተኞችን ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በተለይም
የአእምሮ እድገት ውሱንነት ላለባቸው ዜጎች ልዩ ትኩረት በመስጠት የተግባር ሰዎች እንድንሆን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ
ጥሪ ያቀርባል፡፡

ምንጭ ፡"የአእምሮ እድገት ውሱንነትን መረዳት" በፍቅር የኢትዮጵያ የአእምሮ እድገት ውሱንነት

ብሔራዊ ማህበር የተዘጋጀ ቡክሌት

Please follow and like us:

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *