ደቡብ ኦሞ ዞን በሴቶችና ህጻናት ላይ ለሚፈጸሙ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን አስመልክቶ ከኢፌድሪ ሴ/ህ/ጉ/ሚ/ር እና ከደቡብ ክልል ሴ/ህ/ወ/ጉዳይ ቢሮ ጋር በመተባበር የተዘጋጀ የልምድ ልዉዉጥ መድረክ ተካሄደ።

የጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን በማስወገድ የተሰሩ ሥራች ለመገምግምና በአካል በመገኘት የልምድ ልውውጥ ለማድረግ የሚያስችል የመስክ ጉብኝትና ክልላዊ መድረክ የተካሄደ ሲሆን በ29/7/2015 ዓ.ም የመጀመሪያ ቀን ቆይታ በበና ፀማይና በዳሰነች ወረዳ

በአካል በመገኘት በተለይ የሴት ልጅ ግርዛትና ሚንጊን ለማስቆም የሚያስችሉ ስራዎች እና የታዩ ለውጦች እንዲሁም በአሁኑ ጊዜ እየተፈፀሙ ያሉ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች ተለይተው ባሉ ስራዎች ላይ፣ የክልሉ፣የዞንና የወረዳ አመራሮች እንዲሁም የሀይማኖት እና የጎሳ መሪዎች በተገኙበት ውጤታማ የልምድ ልውውጥ ፕሮግራም ለማካሄድ ተችሏል፡፡

 

በመጀመሪያው ቀን በተካሄደው የልምድ ለውውወጥ ላይ በተገኙ ውጤቶች የሀይማኖትና የጎሳ መሪዎች ሚና፣ የጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች ተከላለካይና አስወጋጅ ኮሚቴ፣የታችኛው መዋቅርና አደረጃጀቶች የነበራቸው ሚና ከፍተኛ መሆኑ መመልክት ተችሏል ፣፡

በተለይ የሴቶች ልጅ ግርዛት ባልተፈጸመባቸው በተመለከተ መጥፎ ስያሜ ይሰጥ የነበረውን በሱዳን ‹‹ሳላማ›› በሚል ድርጊቱን ለማስቆም ወደ አዎንታዊ ስያሜ በመቀየር ውጤት እንዳመጡት በሀገራችንም ሚንጊ የተባለውን በህፃናት ላይ ይፈጸም የነበረውን ጎጂ ልማዳዊ ድርጊት አዎንታዊ ስያሜ በተሰጠው ‹‹ ዋና ናና›› ‹‹ የኛ ልጆች›› በማለት ተግባራዊ በማድረግ በሀገራችንም ሀገር በቀል እውቀቶችና ተሞክሮዎች እንዳለ አመላካች ልምድ ማየት ተችሏል፡፡

 

በሁለተኛው ቀን በተካሄደው መድረክ ክብርት ወ/ሮ አለሚቱ ኡመድ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ፣ አቶ ንጋቱ ዳንሳ የደቡብ ኦሞ ዞን ዋና እስተዳዳሪ ፣የተከበሩ ወይዘሮ ስመኝ ተስፋዩ የዞኑ አፈ ጉባሄ ፣ ወ/ሮ ባይዳ ሙንዲኖ የክልሉ ሴቶችና ህጻናት ቢሮ ሀላፊ፣ ወ/ሮ ምህረት በላይ የዞኑ ሴቶችና ህጻናት መምሪያ ሀላፊ በመሩት መድረክ አቶ ጌትነት አበብል የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ከፍተኛ የሴቶች መብት ጥበቃና ምላሽ ባለሙያ በማህበራዊ ወግ ለውጥ ላይ እንዲሁም አቶ

ጨቡድ ሙሉነህ የዞኑ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ ባለሙያ በዞኑ የተወገዱ፣ የቀነሱ፣ የቀጠሉና ያገረሹ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች በየወረዳው ምን እንደሚመስል ያቀረቡትን ጥናታዊ ሪፖርቶች መነሻ በማድረግ ውይይት በማድረግ በቀጣይ መሰራት ባለባቸው ስራዎች የጋራ ስምምነት የተደረሰ ሲሆን በመጨረሻ ለተገኙት ውጤቶች ሚና ለነበራቸው እውቅና በመስጠት ተጠናቀል ።

ከዚህ ጎን ለጎን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በደቡብ ዞን በነበረው ደርቁ ምላሽ አጋርነት ለማሳየት 1.5 ሚሊየን ብር የሚገመት ምግብ ነክ እና ምግብ ነክ ያልሆኑ ድጋፎችን በማሰባሰብ ለዞኑ ማስረከብ ተችሏል፡፡ለዚህም ድጋፍ አጋርነታቸዉን ያሳዩ ግብረሰናይ ድርጅቶችን በሚንስቴር መ/ቤቱ ስም ምስጋና ቀርቦላቸዋል፡፡

 

Please follow and like us:

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *