የሴቶችን ፍላጎት፤የስነፆታ መብት ማጎልበቻና ችግሮችን የመቋቋም አቅም ማሳደግ ፕሮጀክት ማስጀመርያ ፕሮግራም ተካሄደ፡፡

(ጅማ፤ሚያዝያ 4/2015)የሴቶችን የፆታዊ ፍላጎት እና የስነ-ፆታ መብት በማጎልበት የሚከሰቱ ተፈጥሮአዊም ሆነ ሰው ሰራሽ ችግሮችን ለመቋቋም የሚረዳ የአቅም ማጎልበቻ ፕሮጀክት የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስትሴ/ህ/ማ/ጉ ቢሮ ሃላፊ ተወካይ አቶ አደም ቃሲም፤ የጅማ ዞን ሴ/ህ/ማ/ጉ መምርያ ሃላፊ ወ/ሮ ለጢፋ አባነጋ፤ በፕሮጀክቱ ዙርያ የሚመለከታቸው አካላት እና በሚኒስቴር መ/ቤቱ የሴቶችና ህፃናት ዘርፍ አመራሮች፤በተገኙበት የፒኤች ኢትዮጵያ ኮንሰርትየም (Population Health Ethiopia) ፕሮጀክት ማስጀመርያ ስነስረዓት በጅማ ከተማ ተካሄደ፡፡

 

የፕሮጀክት ማስጀመርያውን የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የሴቶች ማብቃት መሪ ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ወይንሼት ገለሦ ባስተላለፉት መልዕክት ሴቶችን ለማብቃት በተናጥል የሚሰሩ ስራዎች ውጤታማነታቸው አነስተኛ ስለሆነ ሴቶችን በማደራጀት በሁለንተናዊ ዘርፉ አቅምን ማሳደግና በሰውም ሆነ በተፈጥሮ ምክንያት በሴቶች ላይ የሚከሰቱ ችግሮችን መቋቋም እጅግ አስፈላጊ ጎዳይ መሆኑን ጠቅሰው ለዚህ ደግሞ እንደ ፒኤችኢ ኢትዮጵያ በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የሚከሰቱ ችግሮችን ሴቶች የመቋቋም አቅም እንዲፈጠሩ የሚያስችል ተግባራትን ለማከናወን ከሚኒስቴር መ/ቤቱ እና በየደራጃው ከሚገኙ የጅማ ዞን ጋር በመፈራረም መርሃ ግብሩ እንዲጀመር ተደርጓል ብለዋል፡፡ስራ አስፈፃሚዋ አክለውም የሴቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት ለማሳደግ መንግስት የተለያዩ ፖሊሲዎችን ስትራቴጂዎችን፤የተለያዩ የህግ ማእቀፎችን ከአገሪቱ የአስር አመት መሪ እቅድ ጋር በተጣጣመ መልኩ መንግስታዊና መያድ ጋር ለመተግበር እየተንቀሳቀሰ ይገኛል ብለዋል፡፡

 

የኦሮሚ ክልላዊ መንግስትሴ/ህ/ማ/ጉ ቢሮ ሃላፊ ተወካይ አቶ አደም ቃሲም በመርሃ ግብሩ ላይ በመገኘት ባስተላለፉት መልዕክት እንደዞንም ሆነ እንደ ክልል ሴቶች በሁሉም ዘርፍ አቅማቸውን በማሳደግ ተገቢውን መብት ከማስጠበቅ ባሻገር በአገር ደረጃ ውጤታማ እንዲሆኑ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ድጋፉን አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡

 

የጅማ ዞን ሴ/ህ/ማ/ጉ/ መምርያ ኃላፊ ወ/ሮ ለጢፋ አባነጋ በበኩላቸው ቀደም ሲል በፕሮጀክት ድጋፍ በርካታ ሴቶች በሁለንተናዊ ዘርፍ አቅማቸው እያደገ መሆኑን ጠቁመው በዚህ ፕሮጀክት ደግሞ በተለይ በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት በሴት እህቶቻችን እየደረሰ ያለውን አሉታዊ ተፅእኖ ለመቋቋም እጅግ የሚረዳ ፕሮጀክት ነው ብለዋል፡፡

 

 

 

የፕሮጀክቱ መርሃ ግብር በመስክ ጉብኝት ልዩ ልዩ የጓሮ አትክልትን በማልማት ኢኮኖሚያቸውን ባሳደጉ ቤተሰብ የተጀመረ ሲሆን በተደረገው የውይይት መድረክ ላይ ከዚህ በፊት በሴቶች ላይ በኢኮኖሚ፤በጤና በብዝሀ ህይወት ጥበቃና ሌሎች ልዩ ልዩ አውንታዊ ለውጦች በአቶ አበበ ማራ ከቀረቡ በኋላ ታደሚዎች የፕሮጀክቱን ጠቀሚታና በቀጣይ ሊደረግላቸው የሚገባውን ድጋፍና አስተያየት አቅርበው መርሃ ግብሩ ተጠናቋል፡፡

Please follow and like us:

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *