የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የወጣቶች ዘርፍና የመገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን በወጣቶች ዙሪያ በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ።

(ሚያዝያ 18/2015 ዓ.ም ) የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ጋር በወጣቶች ዘርፈ ብዙ ጉዳዬች ላይ በጋራ ለመስራት ተፈራርመዋል።
በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የወጣቶች ዘርፍ ሚኒትር ዴኤታ ወ/ሮ ሙና አህመድ አገራችን ከአፍሪካ በርካታ የወጣቶች ቁጥር ያለባት አገር ናት፣ይህንን ሃይል አቅሙን አውጥቶ እንዲጠቀም በማድረግ የአገር ዘላቂ ዕድገት ማረጋገጥ ይቻላል ያሉ ሲሆን መንግስት ለወጣቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ፖሊሲዎችን በማዘጋጀት፣ የወጣቶች ምክር ቤት በማቋቋምና ሌሎች በርካታ ሥራዎችን በማከናወን ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡
የሚዲያ ተቋማት ዘላቂነት ያለው መረጃ ለማህረሰቡ ተደራሽ በማድረግ አገርን መሸከም የሚችሉ ወጣቶችን ለመገንባትና የአገራችንን ዘላቂ ዕድገት ለማረጋገጥ ሃላፊነታቸውን እንዲወጡ ማድረግ ነው ያሉ ሲሆን የሚዲያ ፎረሙ ዓላማ የሚዲያአካላት ትክክለኛና ዕውነተኛ መረጃ ተደራሽ እንዲያደርጉ ማስቻል እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
በገጠሩ የአገራችን አካባቢዎች ለሚገኙ በርካታ ቁጥር ላላቸው ወጣቶች ሚዲያዎች ተደራሽ መሆን እንደሚገባቸው ጠቁመዋል፡፡
አቶ መሀመድ ኢድሪስ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር የወጣቶች ጉዳይ የአገር ጉዳይ ነው የወጣቶች ጉዳይ የነገዋ ኢትዮጵያ ጉዳይ ነው፣ የነገዋን ኢትዮጵያ የሚያስቀጥሉ ወጣቶችን ማፍራትና የወጣቶችን ስነ ልቦና ከሀሰተኛ መረጃዎችና ከጥላቻ ዕሳቤዎች መጠበቅ ይገባል ብለዋል፡፡
ወጣቶችን ከአደንዛዥ እፅ ሱሰኝነት መጠበቅ ፣ የሞራል ብቃትና ልዕልናን መጠበቅና በመልካም ሞራል በብቁ ቁመና አገርን መሸከም የሚችሉ ወጣቶችን ማፍራት የግድ ይላል ያሉ ሲሆን ሚዲያም የማህበረሰብን ሁለንተናዊ ቁመና የመገንባት ግንዛቤ በመፍጠር ወጣቶችን የመታደግ ሚናወን ሊወጣ ይገባዋል ብለዋል፡፡
ወጣት ተኮር መረጃዎችን ለህብረተሰቡ ተደራሽ ማድረግ፣ቅንጅታዊ አሰራር መፍጠር፣ የመንግስት ተቋማት ሴቶች የወጣቶች ፣ሕፃናት አረጋውያንና ሌሎች ተጋላጭ የማህረሰብ ክፍሎችን ጉዳይ ላይ በጋራ መስራትና ሚዲያ የወጣቶች ስብዕና ግንባታ ላይ በስፋት እንዲሳተፉ ማድረግ የሚዲያ ፎረሙ ከተቋቋመበት ግቦች መካከል ዋና ዋናዎቹ መሆናቸው በፎረም ምስረታው ላይ በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የወጣቶች በጎ ፈቃድ መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ አብይ ኃ/መለኮት አቅርበዋል።
በርካታ የግልና የመንግስት የሚዲያ ተቋማት ከክልሎችና ከከተማ አስተዳደሮች በሚዲያ ፎረም ምስረታው ላይ ተሳትፈዋል።
Please follow and like us:

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *