በጎጅ ልማዳዊ ድርጊቶች የሮድ ማፕ ትግበራ ያለበትን ደረጃ ለማወቅ የክትትል ስራ ተጀመረ

በጎጅ ልማዳዊ ድርጊቶች በተለይም የልጅነት ጋብቻና የሴት ልጅ ግርዛት ለመከላከል የተዘጋጀው ብሄራዊ ፍኖተ ካርታ የአፈፃፀም ሂደት በመገምገም እንዲሁም በየክልሉ ከልጅነት ጋብቻና የሴት ልጅ ግርዛት ነፃ የወጡ ወረዳዎች ነፃ ለመውጣታችው የተሰሩ ስራዎችን እና ተሞክሮዎቻቸውን ጎን ለጎን ያሉበትን ሁኔታ መመልከት ተችሏል።

በምልከታው የታዩ ጠንካራና ደካማ ጎኖችን በመለየት የቀጣይ አቅጣጫ ማስቀመጥ በማስፈለጉ ከሴቶችና ህጻናት ዘርፍና ከእቅድ ክፍልና የሴክተር መ/ቤቶች የተካተቱበት ቡድን በማዋቀር ክልሎችን በአራት ክላስተር በመከፋፈል የሴት ልጅ ግርዛትና የልጀነት ጋብቻ ማስቀረትን በተመለከተ የተከናወኑ አፈጻጸሞችን ለመከታተል፣ ለመደገፍና ግብረ መልስ ለመስጠትና መልካም ተሞክሮዎችን ለመቀመር ፣በክልሎች ከልጅነት ጋብቻና የሴት ልጅ ግርዛት ነፃ የወጡ ወረዳዎች ነፃ ለመውጣታችው የተሰሩ ስራዎችን እና ተሞክሮዎቻቸውን በማየት ያሉበትን ሁኔታ ክትትል በማድረግ በሀግር አቀፍ የተዘጋጀው verification tool በየክልሉ ተግባራዊ ስለሚሆንበት ለመነጋገር የክትትሉ ቡድኑ ስራዎችን ጀምሯል።

ስራዎቹ በተጀመረባቸው ክልሎች ከቢሮ የስራ ሀላፊዎች ጋር በመሆን ማብራሪያና ገለጻ በመስጠት ከሴቶችና ማህበራዊ፣ከጤና፣ከትምህርት ፣ከፍትህ ቢሮዎች መረጃዎች በመሰብሰብ በሮድ ማፕ ትግበራው ምን ስራዎች ተሰሩ፣ምን አልተሰሩም ፣በእያንዳንዱ ሴክተር ምን ተሰራ ፣ምን ያህል በጀት ተመደበ ፣ስራ ላይ ዋለ የሚሉትን በማጠናቀር በሀገር አቀፍ ደረጃ ትግበራው ያለበትን ደረጃ የሚያመላክት ሀገራዊ ሪፖርት በማዘጋጀት በቀጣይ ሊከናወኑ የሚገባቸውን ስትራቴጂያዊ አቅጣጫዎች በማመላከት የውሳኔ ሀሳብ የሚዘጋጅ መሆኑነን ተገለፀ።

Please follow and like us:

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *