“ወጣትነት ለለውጥ፣ ለሥራ ፈጠራና ለአገር ግንባታ ሙሉ ትኩረት ሰጥተው የሚጥሩበት ዕድሜ ነው” ክብርት ደ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር

(ሚያዝያ 21/2015ዓ.ም) ከፍታ የወጣቶች ፌስቲቫል በዩሴ. አይ.ዲ ፣ በአምሪፍ ሂልዝ አፍሪካ፤ከዮኤስኤድ እና ሌሎች አጋር አካላት ትብብር በዛሬው ዕለት በሚኒሊየም አዳራሽ መከናወን ጀምሯል።

በፌስቲቫሉ ላይ ለወጣቶች መልዕክት ያስተላለፉት የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትሯ ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ እንኳን ወደ አፍሪካ መዲና አዲስ አበባ በሰላም መጣችሁ ያሉ ሲሆን ወጣትነት ለነገ ስኬት መልካም ስብዕናን በመላበስ በንቃት የሚጥሩበት የሽግግር ዕድሜ ነው ብለዋል።

ኢትዮጵያ ያላትን ከፍተኛ የወጣቶች ቁጥር በመጠቀም ለማልማት መንግስት ለወጣቶች ጉዳይ ትኩረት በማድረግ ምቹ ፖሊሲዎችን የአሰራር መዋቅሮችን በማዘጋጀት ላይ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

ወጣቶች ለሰላም ትኩረት በመስጠት በምክኒያታዊነት በማመን እራሳቸውን ከጥፋት ሃይሎች መጠቀሚያነት ሊከላከሉ ይገባል ብለዋል።

የወጣቶች ፌስቲቫሉ ወጣቶችን ለመልካም ጉዳዮች ለማነቃቃት የእርስበርስ ግንኙነት ለማሳደግ አዳዲስ መንገዶችን ለማመላከት በመከናወን ላይ ይገኛል።

በፌስቲቫሉ ላይ ከመላው ኢትዮጵያ ከተሞች የተውጣጡ ከ10 ሺህ በላይ ወጣቶች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።

Please follow and like us:

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *