የመረጃ መረብን በመጠቀም በሕፃናትና ታዳጊዎች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን መከላከል በሚቻልባቸው መንገዶች ዙሪያ ሥልጠና በመሰጠት ላይ ይገኛል።

8i(ግንቦት 11/ 2015 ዓ.ም) የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የመረጃ መረብን በመጠቀም በሕፃናትና ወጣቶች ላይ የሚደርሱ ወሲባዊና ሌሎች ትንኮሳዎች መከላከል በሚቻልባቸው መንገዶች ዙሪያ ከፌደራልና ከክልሎች ለተውጣጡ ባለሙያዎች እና የሥራ ኃላፊዎች ሥልጠና በመስጠት ላይ ይገኛል።

በኢትዮጵያ ዕድሚያቸው ከ 12 እስከ 17 ዓመት ከሚሆናቸው የማህበራዊ ሚዲያና ኢንተርኔት ተጠቃሚዎች መካከል 10 በመቶ የሚሆኑት ለወሲባዊ ትንኮሳዎች፣ ማስፈራሪያዎች ተጋላጭ መሆናቸውን ጥናቶች እንደሚያመለክቱ ተገልጿል።

ስልጠናው የማህበራዊ ሚዲያና ኢንተርኔት በመጠቀም የሚፈፀሙ ትንኮሳዎችና ጥቃቶች መለየትና መከላከል በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ ያተኮረ ነው።

በአገራችን እየጨመረ የመጣውን የህፃናትና ወጣቶች የማህበራዊ ሚዲያና ኢንተርኔት ተጠቃሚነት ተከትሎ ወሲባዊ ትንኮሳዎችና ጥቃቶች እየተበራከቱ መጥተዋል ተብሏል።

በአፍሪካ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ጉዳዩ አሳሳቢ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ የተገለፀ ሲሆን ለበርካታ ሕፃናት እራሳቸውን እንዲያጠፉ ላልተፈለጉ ወሲባዊና ሌሎች ጥቃቶች እንዲጋለጡ ምክንያት እየሆነ እንደሚገኝ ተጠቁሟል።

በኢትዮጵያ ሕፃናትና ታዳጊዎችን ከወሲባዊና ጾታዊ ጥቃቶች መከላከል ላይ ትኩረት ሊደረግ ይገባል ተብሏል።

ወላጆችና አሳዳጊዎች የሕፃናትና ታዳጊዎችን የማህበራዊ ሚዲያና ኢንተርኔት አጠቃቀም በቅርበት ሊከታተሉ እንደሚገባ ተጠቁሟል።

የሕፃናትና ታዳጊዎች ማንነታቸውን በውል ለማያቋቸው ግለሰቦችና የማህበራዊ ሚዲያዎች ምስሎችን ከማጋራት ሊቆጠቡ ይገባል የተባለ ሲሆን ጾታዊና ወሲባዊ ትንኮሳዎች በሚያጋጥማቸው ጊዜ ጉዳዩን በአፋጣኝ ለአሳዳጊዎችና ለፍትህ አካላት በማሳወቅ እራሳቸውን ሊከላከሉ እንደሚገባ ተገልጿል።

Please follow and like us:

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *