ሁለተኛው ዙር ሀገር አቀፍ የማህበራዊ ጥበቃ ኮንፈረንስ እየተካሄደ ይገኛል

(አዲስ አበባ፣ ግንቦት 15/ 2015 ዓ.ም) ሁለተኛው ዙር ሀገር አቀፍ የማህበራዊ ጥበቃ ኮንፈረንስ በአፍሪካ ህብረት አዳራሽ እየተካሄደ ይገኛል።

“ማህበራዊ ጥበቃ ለሀገር ግንባታ በኢትዮጵያ” ወይም “Social Protection for Nation Building in Ethiopia ” በሚል መሪ ቃል የሚካሄደው ኮንፈረንስ ለሁለት ቀናት እንደሚቆይ የወጣው መርሀ ግብር ያመለክታል።

በኮንፈረንሱ ከሀገር ውስጥና ከተለያዩ የውጭ ሀገራት የተውጣጡ ባለድርሻና አጋር አካላት እየተሳተፉ ይገኛል።

የኮንፈረንሱ መክፈቻ ስነስርዓት ዛሬ ረፋዱ ላይ በድምቀት የተከናወነ ሲሆን በመድረኩ ላይ ከመርሀ ግብሩ ጋር የተያያዙ መልዕክቶች በተለያዩ አካላት ተላልፈዋል።

ኮንፈረንሱ በዋነኛነት ለልዩ ልዩ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በ2007 ዓ.ም ተቀርጾ ስራ ላይ የዋለው ብሔራዊ የማህበራዊ ጥበቃ ፖሊሲና ፖሊሲውን ለመተግበር የተነደፈው የማስፈጸሚያ ስትራቴጂና የድርጊት መርሀ ግብር ውጤታማ ማድረግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ለመወያየትና የቀጣይ አቅጣጫ ለማስቀመጥ ያለመ እንደሆነ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ኤርጎጌ ገልፀዋል።

ኮንፈረንሱ በባለድርሻ አካላት መካከል ያለውን ቅንጅታዊ አሰራር ለማጠናከርና ሁሉም ለስኬታማ ትግበራ የድርሻውን እንዲወጣ ለማስቻል የበኩሉን እገዛ ያደርጋልም ብለዋል።

Please follow and like us:

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *