“የማህበረሰባችን ችግሮች ለመፍታት በተለይ ተጋላጭ በሆኑ ዜጎች ላይ ኢንቨስት ማድረግ ይገባል” ክቡር ደመቀ መኮንን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር

(አዲስ አበባ፣ ግንቦት 15/ 2015 ዓ.ም) ማህበራዊ ጥበቃ ማህበረሰቡን የሚያስተሳስር፣ ደህንነትንና ሁለንተናዊ እድገትን እውን የሚያደርግ መልህቅ በመሆኑ ችግሮች ለመፍታት በተለይ ተጋላጭ በሆኑ ዜጎች ላይ ኢንቨስት ማድረግ እንደሚገባ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክቡር ደመቀ መኮንን ገለጹ።

ይህን የገለጹት በአፍሪካ ህብረት አዳራሽ ለሁለተኛ ጊዜ በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተካሄደ ያለውን የማህበራዊ ጥበቃ ኮንፈረንስ በይፋ በስጀመሩበት ወቅት ነው።

ክቡር ደመቀ መኮንን በመክፈቻ ንግግራቸው እንደተናገሩት፣ ማህበራዊ ጥበቃ ማህበረሰቡን የሚያስተሳስር ደህንነትንና ሁለንተናዊ እድገትን እውን የሚያደርግ መልህቅ በመሆኑ የማህበረሰባችን ችግሮች ለመፍታት በተለይ ተጋላጭ በሆኑ ዜጎች ላይ ኢንቨስት ማድረግ በእጅጉ እንደሚያሻ በአጽዕኖት አሳስበዋል።

እስካሁንም እያገጠሙ ያሉ ዘርፈ ብዙ ችግሮችን ከመፍታት አኳያ በተለይ የሀገር ውስጥ በጎ ፈቃደኞችን በማደራጀት የህፃናት ማቆያ ማዕከላትን፣ በጎዳና ላይ ኑሮና አዳራቸውን ያደረጉ ዜጎችን መልሶ ለማቋቋም፣ ጥቃት የደረሰባቸውን ሴቶችንና ህጻናትን ስነልቦና በመገንባትና በማቋቋም፣ ጧሪ ቀባሪ የሌላቸውን አረጋውያንን ድጋፍና እንክብከቤ በማድረግ እና ሌሎችን በጎ ተግባራት ጨምሮ የሚሰሩ ስራዎቾ የሚያበረታቱ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ለሁለት ቀናት የሚካሄደው ኮንፈረንስም ፍትሃዊ የኢኮኖሚ እድገትን ለማስፈን የማያስፈልግ የማህበራዊ ጥበቃ Boise ለመምጣት ተጨባጭ ፓሊሲዎችን ለመዳሰስ የሚያስችል አዳዲስ ሃሳቦችን እንደሚያዋጣ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።

“ማህበራዊ ጥበቃ ለሀገር ግንባታ በኢትዮጵያ” ወይም “Social Protection for Nation Building in Ethiopia ” በሚል መሪ ቃል የሚካሄደው ኮንፈረንስ ለሁለት ቀናት እንደሚቆይ የወጣው መርሀ ግብር ያመለክታል።

በኮንፈረንሱ ከሀገር ውስጥና ከተለያዩ የውጭ ሀገራት የተውጣጡ ባለድርሻና አጋር አካላት እየተሳተፉ ይገኛል።

በአሁኑ ወቅትም ከማህበራዊ ጥበቃ ስርዓት ጋር የተያያዙ ልዩ ልዩ ጥናታዊ ጽሁፎ እየቀረቡ ይገኛል።

Please follow and like us:

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *