የማህበራዊ ጥበቃ አገልግሎትን ለሁሉም ተደራሽ ለማድረግ የሚከናወኑ ተግባራት ውጤታማ እንዲሆኑ ባለድርሻ አካላት በቅንጅት እንዲሰሩ ጥሪ ቀረበ

(አዲስ አበባ፣ ግንቦት 15/ 2015 ዓ.ም) እንደሀገር በመተግበር ላይ የሚገኘው የማህበራዊ ጥበቃ አገልግሎት ለሁሉም ተደራሽ እንዲሆን በማስቻል የኢትዮጵያን የብልጽግና ተምሳሌት እውን ለማድረግ በዘርፉ የተሰማሩ ባለድርሻና አጋር አካላት በቅንጅት እንዲሰሩ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ ጥሪ አቀረቡ፡፡

“ማህበራዊ ጥበቃ ለሀገር ግንባታ በኢትዮጵያ” ወይም “Social Protection for Nation Building in Ethiopia ” በሚል መሪ ቃል ለሁለት ቀናት በአፍሪካ ህብረት አዳራሽ እየተካሄደ


በሚገኘው ሁለተኛው ዙር ሀገር አቀፍ የማህበራዊ ጥበቃ ኮንፈረንስ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ እንደተናገሩት፤ በድህነትና በተጋላጭነት ውስጥ የሚገኙትን ዜጎች ለመደገፍ እንደሃገር በረጅም ጊዜ እቅዳችን የማህበራዊ ጥበቃ ስርዓትን ከመዘርጋትና ከመተግበር ባሻገር የስራ እድልን በማስፋት ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ፤ የመሰረታዊ ማህበራዊ አገልግሎቶችን በተለይም የትምህርትና የጤና ሽፋንና ጥራትን በየጊዜው እየሰፋ እንዲሄድ ማድረግ ይገባል።

ይህንን የረጅም ጊዜ እቅድ ለማሳካት በሚካሄዱ ሁሉም ስራዎች በተለይ በድህነትና ተጋላጭነት ውስጥ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች እንደአቅማቸው እንዳይሳተፉ እና ተጠቃሚ እንዳይሆኑ የሚያግዱዋቸውን የፖሊሲ፣ የሕግ፣ የአመለካከት፣ የአተገባበር እና ሌሎች ከቅንጅታዊ አሰራር ጋር የሚስተዋሉ መሰናክሎችን እየፈቱ መሄድ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

በመሆኑም በቀጣይ ለሃገራዊ የኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ እድገት አስተዋፅኦ በማበርከት እንዲሁም የማህበራዊ ጥበቃ ለሁሉም ተደራሽ እንዲሆን በማስቻል የኢትዮጵያን የብልጽግና ተምሳሌት እውን ለማድረግ በዘርፉ የተሰማራን አካላት ተቀናጅተን ትኩረት ሰጥተን እድንሰራ ሲሉ ሚኒስትሯ ጥሪ አቀርበዋል፡፡

Please follow and like us:

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *