የማህበራዊ ጥበቃ ኮንፈረንስ መካሄዱን በዛሬው ዕለትም እንደቀጠለ ይገኛል።

በመድረኩ የኢ. ፌ.ዴ.ሪ.የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የማህበራዊ ዘርፍ ሚኒስትር ደኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ ማህበራዊ ጥበቃ ባለው ሁለንተናዊ ፋይዳ፣ በሀገራችን መተግበር ከጀመረ ወዲህ እስካሁን እየተከናወኑ ባሉ ተግባራትና በተገኙ ውጤቶች እንዲሁም በትግበራ ሂደት ባገጠሙ ተግዳሮቶች እና መፍትሄዎቹ ዙሪያ ገለፃ አድርገዋል።

በተመሳሳይም በማህበራዊ ጥበቃ ላይ ትኩረት ያደረጉ ሌሎች ጥናታዊ ጽሁፎች በተለያዩ አካላት ቀርበዋል።

በቀረቡ ጥናታዊ ጽሁፎች ዙሪያ ሰፊ ውይይት እንደሚካሄድና ከኮንፈረንሱ ተሳታፊዎች ለሚነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች በሚመለከታቸው ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች ምላሽና ማብራሪያ እንደሚሰጥ እንዲሁም የቀጣይ አቅጣጫ እንደሚቀመጥ ይጠበቃል።

Please follow and like us:

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *