የሴቶችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ላይ ትኩረቱን ያደረገ ብሔራዊ የሴቶች ኢኮኖሚያዊ ብቃት ፎረም በዛሬው ዕለት መካሄድ ጀምሯል፡፡

(ግንቦት 23/2015 ዓ.ም)

‹‹የሴቶችን ዕምቅ አቅም ፈጠራና ቴክኖሎጂን በመጠቀም ኢኮኖሚያዊ ብቃትን እናሳካ በሚል መሪቃል በሴቶችና ማህራዊ ጉዳይ ሚኒስቴርና በአጋር አካላት ትብብር በመከናወን ላይ ይገኛል፡፡

በፎረሙ ሴቶች በኢኮኖሚው ዘርፍ ተጠቃሚ እንዳይሆኑ መሰናክል የሚሆኑባቸውን ችግሮች በጥናት በመለየት የመፍትሄ ሀሳቦችን ለማቅረብና የእርስ በእርስ ግንኙነትን ለማዳበር ያለመ እንደገሆነ ተገልጿል፡፡

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚንስትር ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ ሴቶች በምጣኔ ሀብት ረገድ ያላቸውን ተሳትፎ ለማሳደግ መንግስት የተለያ ማዕቀፎችን ተግባራዊ በማድግ ላይ ይገኛል ያሉ ሲሆን በዚህም በርካታ ሴቶች በተለያዩ መስኮች ተደራጅተው ስኬታማ በመሆን ላይ ይገኛሉ ብለዋል፡፡

አክለውም በርካታ ሴቶች ከእራሳቸው አልፈው ለበርካታ ዜጎች የሥራ ዕድል በመፍጠር ላይ ይገኛሉ ያሉ ሲሆን ሴቶች ምቹ ሁኔታ ከተፈጠረላቸው በአገሪቱ በመከናወን ላይ በሚገኘው ብሔራዊ የኢኮኖሚ ግንባታ እንቅስቃሴ ላይ በመሳተፍ የማይተካ አስተዋፅኦ ማበርከት እንደሚችሉ ገልጸዋል፡፡

ሴቶችን በቴክኖሎጂ፣ በገበያ ትስስር ፣ ከወለድ ነጻ ብድርና የእፎይታ ጊዜ ፣ስልጠና ዕጥረት ችግሮችን በዘላቂነት በመፍታት ጥረታቸውን ማበረታታት ይገባል ብለዋል፡፡

የተለያዩ ጥናታዊ ፅሁፎች ቀርበው ውይይት እየተደረገባቸው ሲሆን በተለያዩ የቢዘነስ ዘርፎች ላይ ተሰማርተው በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኙ ስራ ፈጣሪ ሴቶች ምርቶቻቸውን ለዕይታ አቅርበዋል፡፡

በፎረሙ የእንኳን ደህና መጣችሁና የእለቱን ቁልፍ መልዕክት ያስተላለፉት የሚኒስቴር መ/ቤቱ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አለሚቱ አሞድን ጨምሮ የስራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስት ዴኤታ ንጉሱ ጥላሁን ፣ አቶ የሱፍ አድሚኖር የኢትዮጵያ የንግድ ማህበራት ምክር ቤት ምክር ቤት ዋና ስራ አስፈጻሚ፣ እና የ UN women የኢትዮጵያ ተወካይ ሙኩሩቡጋ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

Please follow and like us:

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *