የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሲቢሲዶ ለተሰኘ የአረጋውያን መንከባከቢያ ማዕከል በዛሬው ዕለት የገንዘብና የዓይነት ድጋፍ አድርጓል፡፡

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የአባቶችን ቀን ምክኒያት በማድረግ ለአገራቸው የማይተካ ጉልህ አስተዋፅኦ የነበራቸው አባቶችን የማመስገን መርሃ ግብር በህዝብ ተሳትፎ የተቀነባበረ ዘላቂ የልማት ድርጅት (ሲቢሲዶ) የአረጋውያን መንከባከቢያ ማዕከል በመገኘት የሁለት መቶ ሺህ ብርና አረጋውያንን የጋቢ ማልበስ መርሃ ግብር አከናውኗል፡፡

በመርሃ ግብር ላይ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ማህበራዊ ጉዳይ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ አየለች እሸቴ የአገር ባለውለታ የሆኑ አረጋውያን አባቶችና እናቶችን ለማመስገንና እንኳን ለአባቶች ቀን አደረሳችሁ ለማለትና ከጎናችሁ መሆናችንን ለማሳየት እንወዳለን ብለዋል፡፡

አክለውም አረጋውያን ልምድና ተሞክሮዋቸውን ለተተኪው ትውልድ በማስተማርና በማስተላለፍ፣ ማህበረሰቡን በሚያጋጥሙ ችግሮች ላይ መፍትሔ በማፈላለግ የአካባቢን ሰላምና አንድነት ለማስጠበቅ ረገድ ጉልህ ሚና አላቸው ብለዋል፡፡

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱም መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር በመጣመር በተለየም የአረጋውያንን ዘርፈ ብዙ ችግሮች ለመፍታት ከምንግዜውም በላይ በመስራት ላይ ይገኛል ያሉ ሲሆን መሰልተግባራትን የሚያከናውኑ ግለሰቦችና ድርጅቶችን አመስግነዋል፡፡

 

የአባቶችን ቀንምም ምክንያት በማድረግ ለአረጋውያንን ጋቢ የማልበስ መርሃ ግብር የተከናወነ ሲሆን አባቶች የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል፡፡

Please follow and like us:

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *