6ኛው ቤሔራዊ የአካል ጉዳተኞች አካታችነት ፎረም ተካሄደ፡፡

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚ/ር በአካል ጉዳተኛ ጉዳይ ላይ ከሚሰራ ከዞአ ሲቪል ሶሳይቲ ጋር በትብብር የ6ኛው ቤሔራዊ የአካል ጉዳተኞች አካታችነት ፎረም አካሄደ፡፡

የእለቱን የመክፈቻ ንግግር የደረጉት ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚ/ር የአካል ጉዳተኞች ጉዳይ ስራ አስፈፀሚ አቶ አሳልፈው አመዲን ባስተላለፉት መልዕክት በሀገራችን የሚሰጡ በርካታ አገልግሎቶች የአካል ጉዳተኞችን ሁኔታ ግንዛቤ ውስጥ ያላካተቱ በመሆናቸዉ ሚ/ር መ/ቤቱ ይህንኑ ጉዳይ በመከታተል አካል ጉዳተኞችን ይበልጥ ተጠቃሚ የሚያደርጉ ስራዎች በመንግስትና መንግስታዊ ባልሆኑ ተቋማት ስራዎች እየተሰሩ ቢሆንም ጉዳዩ በሁሉም ተቋት ውስጥ ተካቶ እኩል ተጠቃሚነትን የማረጋገጥ ስራ ይቀራል ብለዋል፡፡

አክለውም ሚ/ር መ/ቤቱ አካል ጉዳተኞችን የተመለከቱ የህግ ማዕቀፎች እንዲዘጋጁና እንዲተገበሩ ከማድረግ ባሻገር ተፈጻሚነታቸዉን ከሚመለከታቸዉ አካላት ጋር በመሆን የመከታተል ስራ በመስራት ላይ የሚገኝ በመሆኑ ህጎችን በመተግበር ደረጃ የአካቶ ትግበራ ስራ ዋና በመሆኑ የተለያዩ ተቋማት ያላቸውን ልምድ ለመለዋወጥና በቀጣይ የመፍትሄ ሀሳቦች ለማመላከት ከዞአ ሲቪል ሶሳይቲ ጋር በመሆን ይህ ፎረም እንዲዘጅ ተደርጓል ብለዋል ፡:

ሚስ ዳውን ሆይሌ የዞአ ካንትሪ ዳይሬክተር መልዕክት ያቀረቡ ሲሆን በመልዕክታቸው የአንድ አገር ሁለንተናዊ እድገት የሚለካው ሁሉን አቀፍ የሆነ የኢኮኖሚያዊ፤ማህበራዊ እና ፖለካዊ እድገት ሲኖር በመሆኑ አካል ጉዳተኞች የአገሪቱ ልማት ተጠቃሚ ከመሆን አንፃር በርካታ ስራዎች እንደሚቀሩና አካል ጉዳተኞችንና ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎችን ያላገናአበ ልማት ቀጣይነት የሌው ይሆናል ብለዋል፡፡ በመሆኑም ማንኛውም ተቋም በሚያከናውነው ተግበር ውስጥ አካል ጉዳተኞችን ያገናዘበና ያሳተፈ መሆን አለበት ብለዋል፡፡

በመርሃ ግብሩ ከአካል ጉዳተኞች ጋር የተያያዙ ጉዳዮች ፅሁፍ ቀርበው ውይይት ተደርጎ አቅጣጫ ተሰጥቶበት የፎረሙ ውይይት ተጠናቋል ።

Please follow and like us:

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *