(ሰኔ 7/2015) የአፍሪካ-እስያ ወጣቶችን የኢኮኖሚና ማህበራዊ ትስስርን ለማጠናከር በጋራ መስራት ይገባል-ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ

የአፍሪካ-እስያ ወጣቶችን የኢኮኖሚና ማህበራዊ ትስስርና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በጋራ መስራት እንደሚገባ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ ገለጹ።

በ”ኦየስ-ግሎባል ፋውንዴሽን” አዘጋጅነት ከአፍሪካና እስያ አህጉር የተውጣጡ ወጣቶች ፎረም ማጠናቀቅያ ላይ የኦየስ-ግሎባል ፋውንዴሽንን እንዲጠናከር ድጋፍ በመድረግ ተሸላሚ የሆኑትና በክብር እንግድነት ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፋት ክብርት ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ የአፍሪካና የእስያ ወጣቶች በስራ ፈጠራ፣ በጤና፣ በአካባቢያዊ የአየር ንብረት ለውጥ፣ በሰላም፣ በበጎ ፈቃደኝነት እና በሌሎች ርዕሰ ጉዳዮች እውቀትና ልምድ እንዲጋሩ በማድረግ ወጣቶችን ለማብቃት ታሳቢ ያደረገ መሆኑ ገልፀው ወጣቶች በሀገራት የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካና ማህበራዊ ተሳትፎ ላይ ቁልፍ ሚና ያላቸው መሆኑን አንስተዋል።

በመሆኑም ወጣቶች በአመራር፣ በስራ ፈጠራ፣ በኢኮኖሚና ሰላም በማስፈን ሁሉን አቀፍ ተሳትፎ እንዲኖራቸው ቀጣይነት ያለው ስራ በጋራ መስራት ይገባል ብለዋል።

በእለቱ የአፍሪካና እስያ ሀገራት ዲፕሎማቶችና ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል። በቀጣይ ዓመት ኢንዶኔዥያ ይህንኑ መድረክ ለማሰተናገድ ርክክብ ተደርጓል ።

Please follow and like us: