የሳውዲ አረቢያ መንግስት ለስደት ተመላሾች ማቋቋሚያ የሚሆን የ1ሚሊየን ዶላር የድጋፍ ፕሮጀክት ይፋ አደረገ።

የሳውዲ አረቢያ መንግስት ለስደት ተመላሾች ማቋቋሚያ የሚሆን የ1ሚሊየን ዶላር የድጋፍ ፕሮጀክት ይፋ አደረገ።


(ህዳር 5/2016)ድጋፉ በተለያዩ ምክንያቶች ከሳውዲ አረቢያ የሚመለሱ 18ሺ 1መቶ ዜጎችን ለመቀበል፣ በመጠለያ ለሚያርፉ ተመላሾች ምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ አገልግሎቶችን ለመስጠት እና ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመከላከል የሚያስችሉ የህብረተሰብ ንቅናቄና ግንዛቤ ለመፍጠር የሚውል ነው።

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ የሳውዲ አረቢያን መንግስት ላደረገው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ድጋፉ ለኢትዮጵያዊያን ስደት ተመላሾች ለሚደረገው የሰብአዊና ማህበራዊ አገልግሎት እንዲሁም ኢ-መደበኛ ፍልሰትን ለመከላከል ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚያደርግ ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ የሳውዲ አረቢያ አምባሳደር ፉሃድ ኦባይዱላህ (ፒ ኤች ዲ) የሳኡዲ አረቢያ መንግስት ወደፊትም ድጋፍ ማድረጉን የሚቀጥልና በትብብር የሚሰራ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

ፕሮጀክቱን ተግባራዊ የሚያደርጉት የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ፣ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ የአደጋ ስጋትና ስራ አመራር ኮሚሽን እና የዓለም አቀፉ የፍልሰት ድርጅት በመተባበር ነው።

የገንዘብ ድጋፉ ፕሮጀክቱ የንጉስ ሳልማን የሰብአዊ ድጋፍና እርዳታ ማዕከል በዓለም አቀፉ የፍልሰት ድርጅት (IOM) በኩል ተደራሽ የሚሆንና በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ተግባራዊ የሚደረግ ነው።

Please follow and like us: