ኢ- መደበኛ ፍልሰትን ለመከላከልና ደህንነቱ የተጠበቀ የስራ ዝውውር እንዲኖር የኢትዮጵያ መንግስት እያደረገ ያለውን ጥረት ዓለም አቀፍ ተቋማት እንዲደግፉ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ ጠየቁ።


(አዲስ አበባ፣ ሕዳር 6፣ 2016 ዓ.ም) በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር፣ ዩ ኤ ን ውመን፣ በዓለም አቀፉ የፍልሰት ድርጅት እና የጀርመን መንግስት በጋራ የሚተገበር “ፍልሰትን ለሴቶች ደህንነቱ የተጠበቀ ማድረግ” የሚል ፕሮጀክት 2ኛ ምዕራፍ ይፋ ተደርጓል።

ፕሮጀክቱ ሴቶች ከኢትዮጵያ ወደ ሌሎች ሀገሮች፣ ከሌሎች ሀገሮች ወደ ኢትዮጵያ እና በኢትዮጵያ በኩል ዝውውር ሲያደርጉ ደህንነታቸው የተጠበቀ እና ህጋዊ እንዲሆኑ ማድረግን ታሳቢ ነው።

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ በህገ ወጥ ፍልሰት ውስጥ ሴቶች ለተለያዩ አደጋዎች ተጋላጭ በመሆናቸው ደህንነቱ የተጠበቀ ፍልሰት እንዲኖር ኢትዮጵያ በትኩረት እየሰራች መሆኑን ተናግረዋል።

ደህንነቱ የተጠበቀ ፍልሰት እንዲኖር ቅንጅታዊ አሰራር ያስፈልጋል ያሉት ሚኒስትር ዴኤታዋ ዓለም አቀፍ ተቋማት ኢትዮጵያ የጀመረችውን ጥረት እንዲደግፉ ጠይቀዋል።

በኢትዮጵያ የ ዩ ኤን ውመን ሀገራዊ ተወካይ ወ/ሮ ሴሲሌ ሙካሩቡጋ ህጋዊ ፍልሰት እንዲኖር እና የሴቶችን ተጋላጭነት ለመቀነስ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ አረጋግጠዋል።

ከኢትዮጵያ ወደ ሌሎች ሀገሮች በሚደረግ ፍልሰት ውስጥ 50 ከመቶዎቹ ሴቶቻ ናቸው።

ፍልሰትን ለሴቶች ደህንነቱ የተጠበቀ ማድረግ በሚል የተጀመረው ፕሮጀክት ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር፣ ዩ ኤ ን ዉመን፣ በዓለም አቀፉ የፍልሰት ድርጅት (IOM) እና የጀርመን መንግስት ጋር በትብብር የሚተገበር ነው፡፡

Please follow and like us: