በብለልሃት ፣በቁርጠኝነትና በቅን ልቦና በመነሳት ሃገርንም ሆነ ወገንን መጥቀም የሚቻልበት ወቅት አሁን መሆኑ ተገለጸ

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከሚያስተባብራቸው ከሁሉም ክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች ቢሮ ሃላፊዎችና ከፍተኛ ባለሙያዎች ጋር በቀጣዮቹ 100 ቀናትና የ2014 ዓም እቅድ ላይ በጋራ ለመወያየት ባዘጋጀው የምክክር መድረክ ክብርት ሚኒስትሯ ዶር ኤርጎጌ ተስፋዬ እንደገለጹት ተቋሙ ከተሰጠው ተግባርና ሃላፊነት አንጻር በብልሃት፣ በቁርጠኝነትና በቅን ልቦና በመነሳት ሃገርንም ሆነ ወገንን መጥቀም የሚቻልበት ጊዜ አሁን ነው ::
ሚኒስቴሯ አክለውም ተቋሙ በአዲስ አደረጃጀት ከተዋቀረ ጀምሮ ቀደም ሲል የነበሩትን ሁለት ተቋማት በማዋሃድ፣ የ10 ዓመቱን የልማት እቅድ፣የ2014ዓም እና የቀጣዮቹን 100ቀናት እቅድና የጋራ በማድረግ፣ምቹ ስራ አካባቢን በመፍጠርና አዲስ መዋቅሮችን በአዲስ መልክ በማዘጋጀት ወጥ በሆነ አሰራርና አደረጃጀት ተግባርና ሃላፊነቱን በብቃት ለመወጣት ጥረት እያደረገ ነው ብለዋል፡፡
በውይይቱ ባለፉት ሶስት ወራት በተከናወኑ ዋናዋና ተግባራት ሰፊ ውይይት የተካሄደ ሲሆን በተጨማሪም ከሌሎች ሴክተር ተቋማት፣ መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶችና ከሴቶችና የወጣቶች አደረጃጀቶች ጋር ያለውን ቅንጅትዊ ለማጠናከር የሚረዱ ሃሳቦች እንዲሁም ያጋጠሙ ችግሮችና የተወሰዱ የመፍትሔ እግርምጃዎች ላይ ሰፊ ውይይት ተካሂዷል፡፡
Please follow and like us:

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *