የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ለዜጎች የሚሰጠውን የማህበራዊ አገልገሎት በዲጂታል መልክ ለማድረግ የሚያስችለውን ስርዓት ሊዘረጋ ነው።

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ለዜጎች የሚሰጠውን የማህበራዊ አገልገሎት በዲጂታል መልክ ለማድረግ የሚያስችለውን ስርዓት ሊዘረጋ ነው።

ሚኒስቴሩ ከዓለም አቀፉ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት እና ከብሄራዊ ዲጂታል መታወቂያ አገልግሎት ጋር ስርዓቱን ለመዘርጋት የሚያስችለውን የትብብር ስምምነት ተፈራርሟል፡፡

ስምምነቱ የሶፍትዌር ዝርጋታ፣ የቴክኒል ድጋፍ እና የአቅም ግንባታን ያካተተ ሲሆን መንግስት ለዜጎች የሚሰጠውን የማህበራዊ አገልገሎት ዲጂታል በማድረግ ቀልጣፋ የመረጃ ልውውጥ እንዲኖር ለማስቻል ነው።

ስርዓቱ ሲዘረጋ ከብሄራዊ መታወቂያ ጋር እንዲተሳሰር የሚደረግ ሲሆን በማህበራዊ አገልግሎት አሰጣጥ ውስጥ የሚያጋጥም ድግግሞሽን በማስቀረት ፍትሃዊነትን ለማረጋገጥ ያስችላል።

ዲጂታል እና አካታች የማህበራዊ ጥበቃ ስርዓቶችን በመዘርጋት እና በመተግበር ከመንግስት ወደ ተጠቃሚዎች የሚደረጉ ክፍያዎችን/ድጋፎችን ለማሳለጥ እና መረጃን ወደ አንድ ማዕከል በማምጣት የቁጥጥርና ክትትል ስራዎችን ለማጠናከር አይነተኛ ሚና ይጫወታል፡፡

ስርዓቱ ሁሉንም አይነት የማህበራዊ ጥበቃ አገልግሎቶችን በተለያዩ አማራጮች ተደራሽ ለማድረግ፣ ዘላቂ፣ ወጪ እና ጊዜ ቆጣቢ እንዲሁም ሁሉንም የማህበረሰብ ክፍሎች አካታች የሆነ ስርዓት ለመዘርጋት ያስችላል ተብሏል

Please follow and like us: