እስካሁን በተከናወነ ሥራ ከጎዳና የተነሱ ወገኖች ቁጥር 54 ሺህ 288 ደረሰ

በጎዳና የሚገኙ ወገኖችን ለማንሣት እንደ ሀገር እስካሁን በተከናወነው ሥራ የተነሺዎች ቁጥር ከነበረበት 39 ሺህ 082 ወደ 54 ሺህ 288 ከፍ ማለቱን የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የማህበራዊ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ሁሪያ አሊ አስታወቁ፡፡

በተጠናቀቀው ግማሽ ዓመትም 19 ሺህ 756 ወገኖችን ከጎዳ በማንሳት የማቋቋም ሥራ መከናወኑን ነው ሚኒስትር ዴኤታዋ የተናገሩት፡፡

ባለፉት ሥድስት ወራትም በከተማ ልማታዊ ሴፍትኔትና ሥራ ፕሮጀክት 4 ሺህ 550 እንዲሁም ከክልሎችና ከፌዴራል ከተማ አሥተዳደሮች በተገኘ በጀት 15 ሺህ 206 ወገኖችን ከጎዳና ላይ በማንሳት የተቋም አገልግሎት እንዲያገኙ፣ ወደ መጡበት አካባቢና ቤተሰቦቻቸው ተመልሰው እንዲቋቋሙ መደረጉን ገልጸዋል፡፡

ይህን ተከትሎም ከጎዳና ላይ የተነሱ፣ በአገልግሎት መስጫ ተቋማት የተለያዩ አገልግሎቶችን ያገኙ እና ወደ ቤተሰቦቻቸው (ማሕበረሰቡ) የተቀላቀሉ፣ የተዋሃዱና የተቋቋሙ ወገኖችን ቁጥር ከነበረበት 49 ሺህ 82 ለማድረስ ታቅዶ 54 ሺህ 288 ማድረስ ተችሏል ብለዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደርም ለሥራው ትኩረት ሰጥቶ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት በመሥራቱ ዕቅዱን ከታሰበው በላይ ማሳካት ተችሏል ነው ያሉት፡፡

Please follow and like us: