የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ጋር በጋራ ለመስራት በሚስችሏቸው ጉዳዮች ዙሪያ ተወያዩ፡፡

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚንስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ( ዶ/ር) የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ዛዲግ አብረሃ ባደረጉት ውይይት አብሮ ለመስራት የሚያስችል የአጋርነትና የትብብር መስኮችን ቃኝተዋል።

በውይይቱ ላይ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚንስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ( ዶ/ር) ለተሰጠው ማብራሪያ ከልብ አድናቆታቸውን ገልፀው የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ አሁን ካለው አቅም በተጨማሪ ከሌሎች የስልጠና ተቋማት ጋር የሚወዳደር የአመራር ልማት ማዕከል እና መሠረተ ልማት ለመገንባት የሚደርገውን ተነሳሽነት አድንቀዋል።

ሚንስትሯ አክለውም በወጣቶች ስራ ፈጠራ፣ በሴቶች አቅም ግንባታና ኢኮኖሚ ተጠቃሚነት፣ የአፍሪካ ሴቶች ፕሮግራም፣ የወጣቶች የፓን አፍሪካን ጉባኤ፣ አፍሪካዊ ማሳያ(african simulation) ፣አፍሪካ ኤስያ የወጣቶች ጉባኤ፣ከብሪክስ (BRICS) ሀገራት ጋር የወጣቶችን ግንኙነት ከማጠናከር አንፃር፣ የአለም አቀፍ ሁነቶችን ወደ ማእከሉ ማምጣት በሚቻልበት ሁኔታ ዙሪያ ከሚኒስቴሩ ተልእኮ እና ግብ ጋር በሚጣጣሙ ሌሎች ሰፊ ስራዎች ላይ መሳተፍ አስፈላጊ መሆኑን አፅንዖት ሰጥተዋል።

የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ዛዲግ አብረሃ በበኩላቸው የአመራር ልማት ፕሮግራሞች እና የሶስት አመት ስትራቴጂ አጠቃላይ እይታን አቅርበዋል።

የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ የአፍሪካ ወጣቶች በአህጉር አቀፍ ልማት ላይ እንዲወያዩ እና አፍሪካን ያማከለ አካሄድን በመጠቀም የስራ ፈጠራ ችሎታቸውን እንዲያሻሽሉ መድረክ ሆኖ እንደሚገለግልና ሚኒስትር መስሪያቤቱም ለሚያከናውናቸው ዘርፈ ብዙ ስራዎች ማዕከሉ ተመራጭ ሆኖ እንደሚያገለግል ጠቅሰዋል፡፡

 

ዘጋቢ ስለእናት እስከዳር

Please follow and like us: