የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር እና ዩኤን ዉሜን (un-women) በጋራ በስርዓተ-ፆታ እኩልነት እና ሴቶች ማብቃት ላይ የሚሰሩ ስራዎችን አጠናክሮ ለመቀጠል የሚያስችላቸውን ስምምነት አደረጉ፡፡

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚንስትር ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ በውይይቱ ላይ እንደገለፁት ዩኤን ዉሜን (un-women) ብሄራዊ የስርዓተ-ፆታ እኩልነት ፖሊሲ እና የሴቶች ማብቃት ፖሊሲ ልማት ፣የስርዓተ-ፆታ እኩልነት ፍኖተ ካርታ ፣ፆታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች ላይ የሚሰጠውን ድጋፍ እና ምላሽን ጨምሮ ለወሳኝ መደበኛ ሂደቶች የቴክኒክ እና የገንዘብ ለሚያደሰርገው እገዛ አመስግነዋል፡፡

በተጨማሪም የስርዓተ-ፆታ እና ሌሎች የማህበራዊ ማካተት ጉዳዮች ላይ እገዛቸውንና ልምዳቸውን እንዲያካፍሉ ሚንስትሯ ጠይቀዋል፡፡ በውይይቱ ሴቶችን በኢኮኖሚ የማብቃት ፕሮግራሞች ዙሪያና የሴቶች የአመራር መዋቅር ለማቋቋም የሚያስችል የጋራ መግባባት ላይ ደርሰዋል፡፡

ወ/ሮ ሲሲል መኩሩቡጋ (Ms. Cecile Mukarubuga, UN Women Country Representative, እንደገለፁት በሁሉም ደረጃዎች የሴቶችን አመራር ተሳትፎ ማሳደግ; ሴቶች በሰላም ግንባታና እና የሴቶችን ኢኮኖሚያዊ አቅም ለማሳደግ ውጤታማ ተሳትፎ ማድረጋቸውን ማረጋገጥ ትኩረት የሚሰጡባቸው መስኮች መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡

ዩኤን ዉሜን (un-women) በኢትዮጵያ ስራ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ በተለያዩ  ጉዳዮች ዙሪያ ከሚኒስቴር መስራያቤቱ ጋር በትብብር እየሰራ እንደሚገኝ ይታወቃል።

Please follow and like us: