ዜና እረፍት!

የኢፌዴሪ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የስራ ባልደረባ የነበረው ወጣት መኳንንት ጌታነህ ባደረባቸው ድንገተኛ ህመም ከዚህ ዓለም በሞት በመለየታቸው የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ይገልጻል።

ወጣት መኳንንት ጌታነህ ላለፉት አመታት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን በሙያቸው ሲያገለግሉና የበኩላቸውንም ድርሻ በቅንነት ሲወጡ መቆየታቸው ይታወቃል።

ስነስርዓተ ቀብራቸው በነገው ዕለት ማለትም ጥር 25 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 6:00 ሰዓት ቤተሰቦቻቸው፣ ወዳጅ ዘመዶቻቸውና የሙያ አጋሮቹ በተገኙበት ቤላ አካባቢ በሚገኘው በደብረ እንቁ ቅድስት ልደታ ቤተክርስቲያን እንደሚፈጸም የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

በመሆኑም የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የስራ ኃላፊዎችና የስራ ባልደረቦች በወጣት መኳንንት ጌታነህ ድንገተኛ ህልፈት የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እየገለጽን፤ ፈጣሪ ለመላው ቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸውና ለሙያ አጋሮቻቸው መጽናናት እንዲሰጥልን ከልብ እንመኛለን፡፡

ፈጣሪ ነፍሳቸውን በአጸደ ገነት ያኑርልን!!

Please follow and like us: