ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሰጡት ማብራሪያ ዋና ዋና ነጥቦች፦

👉የለውጠን መንግስት የሚያኮራው ነገር ካለ ብድር ላይ ያለው አቋም ነው፤

👉 በአራጣ የሚመጣ ብድር ይቅርብነ ብለን ባለፉት አመታት አንድም ብር በኮሜርሻል ሎን አልወሰድንም፤ ይልቁንም 9 ነጥብ 9 ቢሊዮን ዶላር ከፍለናል፤

 

👉 እኛ ስንመጣ እዳችን የጂዲፒያችን 32 በመቶ ነበር፤ አሁን 17 በመቶ አድርሰነዋል፤

👉 9 ነጥብ 9 ቢሊዮን ዶላር እዳ የከፈለ፤ 7 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ገቢ እቃ የገዛ መንግስት 33 ሚሊዮን ዶላር የወለድ ክፍያ መክፈል አቃታት ቢባል ቀልድ ነው፤

👉33 ሚሊዮን ዶላር ማለት የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሁለት ቀን ገቢ ነው፤

👉 የዘንድሮ ማዳበሪያ ግዥ አልቋል፤ ከፊሉ ገብቷል፤ ከፊሉ እየተጓጓዘ ነው፤ አምና ግን በዚህ ሰአት ገና ግዥ ላይ ነበርን፤

👉 እንደ ደቡብ ምዕራብ ያሉ አዳዲስ ክልሎች ከሀብት አንጻር ለሌላው የሚተርፉ ናቸው፤

👉 አገር የምትበለጽገው በፕሮጀክት ነው፤ አገር የፕሮጀክቶች ድምር ውጤት ነው፤

👉 የአድዋ ፕሮጀክት እዚህ የደረሰው ክብር ከንቲባዋና ቡድናቸው በየቀኑ ማታ አምስት አምስት ሰዓት እየገመገሙ ስለመሩት ነው፤ ያለሥራ የሚመጣ ለውጥ የለም፤

👉 ልማት አደናቃፊዎች ብዙ ናቸው፤ ቅርስ ይጠበቃል፤ በቅርስ ስም ያለ ህንጻ ቻይናም አሜሪካም ይፈርሳል፤ እዚህም ይፈርሳል፤

👉 የስፖርት ውርርድ (ቤቲንግ) ላይ የተሟላ መረጃ ስለሌለኝ ብሄራዊ ሎተሪ አጥንቶ ያቀርቧል፤

👉 የኢትዮጵያን ብሔራዊ በሚያስጠብቅ መልኩ ከሁሉም ጋር በሁሉም ጫፍ እንሰራለን፤

Please follow and like us: