“ከዕዳ ወደ ምንዳ” በሚል ርዕስ ላይ ለፌዴራል መንግስት ሰራተኞች የተዘጋጀውን የስልጠና መርሃ-ግብር መነሻ በማድረግ ለሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሰራተኞች አጠቃላይ ስልጠና ተሰጠ።

ስልጠናው በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ በውይይቱ በመጀመርያ ቀን ውሎው ሀብት የመፍጠር ጉዟችን፣ እያጋጠሙን ያሉ ተግዳሮቶችና ቀጣይ አቅጣጫዎች በሚል ርእስ የተዘጋጀ የውይይት መነሻ ሰነድ አቅርቦ ተወያይቷል።የሰነዱ ዋነኛ አላማም ሰራተኛው በመንግስት ወቅታዊ ዋና ዋና የልማትና የሠላም አጀንዳዎች ዙሪያ ማለትም ፀጋችንን በአግባቡ ተጠቅሞ ከድህነት ለመላቀቅ በሚደረገው እንቅስቃሴ ላይ በተገኙ ምርጥ ተሞክሮዎች፣ጉድለቶች እና ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን በመወያየትና በመመካከር የተሻለ ግንዛቤ መፍጠር መሆኑ ተገልጿል።

በሁለተኛው ቀን ውሎም በክብርት ሙና አህመድ የወጣቶች ዘርፍ ሚንስትር ድኤታ አገልጋይና ስልጡን ሲቪል ሰርቪስ ለኢትዮጵያ ብልፅግና በሚል ርእስ ስልጠናዉ የተሰጠ ሲሆን፣የስልጠናው ዋነኛ ዓላማማም ህዝቡን አገልጋይና ስልጡን ሲቪል ሰርቪስ ከመገንባት እና ከመምራት አኳያ ያለንበትን ሁኔታ ከመንግስት ሠራተኛ ጋር በመወያየት የመንግስትን የመፈፀም አቅም ወደ ተሸለ ደረጃ በማሸጋገርና የህዝቡን ሁሉን አቀፍ ተሳትፎ ዕውን በማድረግ ፍትሃዊና ዘላቂ ተጠቃሚነቱን ለማረጋገጥ ያለመ ነው፡፡

በመሆኑም አገራችን አሁን ያለችበት ምዕራፍ ከእዳ ወደ ምንዳ የምንሸጋገርበት እና ለዚህም የመንግስት ሰራተኛው ያለንን ሀብት በአግባቡ አውቆ ተግቶ ለመስራት እንዲችል እና ለዚህ እንቅፋት የሆኑ ጉዳዮችን ለይተን በጋራ መታገል እንደሚገባን ግንዛቤ በመፍጠር መላው ህዝባችን የተስፋ ስንቅና ጉልበት በመያዝ የአገራችንን እድገት እንዲያሳካ ማድረግ መሆኑም ተጠቅሷል።
Please follow and like us: