የአፍሪካ ወጣት መሪዎች ዓለም አቀፍ የዲፕሎማሲ ኮንፈረንስ የመክፈቻ ስነስርዓት ተካሄደ።

የአፍሪካ ወጣት መሪዎች ዓለም አቀፍ የዲፕሎማሲ ኮንፈረንስ (AYLDC) በስካይ ላይት ሆቴል ተካሄደ። ኮንፈረንሱ የተዘጋጀው የኢፌዴሪ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ወጣቶች ውይይት ለሰላም ማህበር (EYDPA) እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ነው።

በኮንፈረንሱ ላይ ንግግር ያደረጉት የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ በአህጉሪቷ የወጣቶችን ሁሉን አቀፍ ተሳትፎ በማረጋገጥ የምንመኛትን አፍሪካ እውን ለማድረግ መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል:: በተለይም በአመራርነት ላይ ያሉ ወጣቶችን በማበረታታትና ተሳትፎአቸውን በማሳደግ አህጉሪቷን ወደ ላቀ ደረጃ ማሸጋገር ይገባል ብለዋል:: ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዚሁ ወቅት እንዳሉት የነገዋ አፍሪካ እድል ፈንታ የሚወሰነው አሁን ላይ ባሉ ወጣቶች እንደሆነ ጠቁመዋል::

በመሆኑም የአፍሪካ ወጣቶች በፓን አፍሪካኒዝም እሳቤ በጋራ የበለፀገች አፍሪካን ለመገንባት ሊሰሩ እንደሚገባ አጽኖት ሰጥተዋል:: ኮንፈረንሱ ስለአመራርነት፣ ስለዲፕሎማሲ እና ስለ ዓለም አቀፋዊ ግንኙነት ሰፊ ውይይት ለማካሄድ ያለመ እንደሆነ የኢትዮጵያ ወጣቶች ውይይት ለሰላም ማህበር ዳይሬክተር ወጣት ኢንጂነር ጫላ አሰፋ ገልጿል። ኮንፈረንሱ የወደፊት የለውጥ መሪዎች እና ወኪሎች የሆኑት የአፍሪካ ወጣቶች ድምጽ፣ አመለካከት እና ፍላጎት በሰፊው የሚደመጥበትና የሚንጸባረቅበት  ይፈጥራል ብሏል። ወጣት መሪዎች ከዲፕሎማቶችና ከመንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር ግንኙነት ለመፍጠርና ተሞክሮ ለመለዋወጥ መድረኩ የበኩሉን እገዛ ያደርጋልም ብለዋል።

ኮንፈረንሱ ለሚቀጥሉት ሁለት ቀናት የሚቆይ ሲሆን በመድረኩ ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት፣ ዩኒቨርስቲዎችና ከሲቪክ ማህበራት የተውጣጡ ከ200 በላይ ወጣት መሪዎች እየተሳተፉ ይገኛል። በዕለቱ ወጣቶችን ለማብቃት እና በሌሎችም፦ መስኮች የላቀ ስራ ለሰሩ አካላት እወቅና ተሰጥቷል።

Please follow and like us: