የሴቶችና ማህ ዳይ ሚኒስቴር ለመካኒሳ መስማት የተሳናቸው ትምህርት ቤት የ ሦሥት መቶ ሺ ብርና የተለያዩ ቁሳቁሶች ድጋፍ አደረገ፡፡

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ለመካኒሳ መስማት የተሳናቸው ትምህርት ቤት የ ሦሥት መቶ ሺ ብር፤ለ 258 ለሚሆኑ መስማት ለተሳናቸው ተማሪዎች የተለያዩ ቁሳቁሶች፤ አጋዥ የማዳመጫ መሳሪያዎችን ድጋፍ አደረገ፡

በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚንስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) በድጋፍ ስነስርአቱ ላይ እንደገለጹት መንግስት የዜጎችንና የአካል ጉዳተኞችን ማህበራዊ ችግሮች ለመቅረፍ የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ ከነዚህም ስራዎች ውስጥም ከተለያዩ አጋር ድርጅቶ ጋር በመተባበር ሀብት በማሰባሰብ ለአካል ጉዳተኞችና የማህበራዊ ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች ተደራሽ የማድረግ ስራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ሚኒስትሯ አክለውም ሚኒስቴር መስሪያቤቱ ድጋፍ ለሚያሥፈልጋቸው አካል ጉዳተኞችና ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎች በተለያዩ ጊዜያት ድጋፍ ማድረጉን አስታውሰው ለዚህ አናጋፋ ትምህርት ቤትም ይህን መሰል ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል፡፡

 

መካኒሳ መስማት የተሳናቸው ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር አቶ ሙሴ አለማየሁ በበኩላቸው ለተደረገላቸው ድጋፍ አመስግነው ትምህርት ቤቱ ከተማሪዎች ምገባ ፣የትራንስፖርት ፣የመማሪያ መፅሀፍት ፣ ሌሎች መስማት ለተሳናቸው የሚያገለግሉ ምስላዊ ትምህርትን የሚያግዙ ቁሳቁሶች በቅንጅት መንግስትና ሌሎች ባለድርሻ አካላት መሰል ትምህርት ቤቶች ላይ የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል ።

ዘጋቢ ስለእናት እስክንድር

Please follow and like us: