2ሺህ የሚሆኑ የቅድመ ወሊድና የወሊድ አገልግሎት መስጫ ማእከላትን በኢትዮጵያ ለመገንባት የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ፡፡

ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ እና በሩስያ የፓን አፍሪካ የመንግስትና የግል አጋርነት የልማት ማዕከል 2ሺህ የሚሆኑ የቅድመ ወሊድና የወሊድ አገልግሎት መስጫ ማእከላትን በኢትጵያ ለመገንባት የሚያስችል የሶስትዮሽ የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ፡፡

ስምምነቱ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴርና ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በሩስያው የፓን አፍሪካ የመንግስትና የግል አጋርነት የልማት ማዕከል ጋር በመተባበር ከሩስያ መንግስት ጋር ረጅም ዘመናትን ያስቆጠረውን የወዳጅነትና በትብብር የመስራት ባህል የሚያዳብር መሆኑን ሚኒስትሯ ኤርጎጌ ተስፋዬ(ዶ/ር ) ገልጸዋል።

 

 

ስምምነቱ የእናቶችንና የጨቅላ ህፃናትን ህይወት ለማሻሻል የሚረዳ በአይነቱ በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ሚድ ዋይፈሪ ማእከል እንደሚሆን ተጠቅሷል፡፡ ለዚህም ኢትዮጵያ በመመረጥዋ በሩስያው የፓን አፍሪካ የመንግስትና የግልአጋርነት የልማት ማዕከልን እና ቦንጋ ዩኒቨርስቲም ይህን ዕድል ወደ ሐገር ውስጥ እንዲመጣ ላበረከተው አስተዋፅኦ ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር ) የላቀ ምስጋናቸውን ገልፀዋል፡፡

 

የቦንጋ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ጴጥሮስ ወ/ጊዮርጊስ በበኩላቸው የቅድመ ወሊድና የወሊድ አገልግሎት መስጫ ማእከሉ በተጨማሪነትም አረጋውያንን ለመደገፍ የሚያስችል አገልግሎቶችንም እንደሚያካትት ገልጸዋል፡፡

በሩስያው የፓን አፍሪካ የመንግስትና የግል አጋርነት የልማት ማዕከል ዋና ስራ አስፈጻሚ ሚስ ኦክሳና ማያሮቫ በበኩላቸው የሩስያ መንግስትና ድርጅቱ ይህንን ማእከል በኢትዮጵያ ለመገንባት ብሎም ሌሎች የልማትና የትብብር መስኮች ላይ አብሮ ለመስራት ያለውን ተነሳሽነት ጠቅሰዋል፡፡

Please follow and like us: