የተቋሙ ሠራተኞች በሀገራዊና ተቋማዊ እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ውይይት አካሄዱ

የኢፌዴሪ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አመራሮችና ሠራተኞች በሀገራዊና ተቋማዊ እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ውይይት አካሂደዋል።

ሪፖርቱን ያቀረቡት የወጣቶች ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታዋ ክብርት ወ/ሮ ሙና አህመድ የ2016 በጀት ዓመት ባለፉት ስድስት ወራት በማይክሮና ማክሮ ደረጃ እንደሀገር በየዘርፉ የተከናወኑ ተግባራትን እቅድ አፈጻጸም በሰፊው አብራርተዋል። በዚሁ ወቅት፥ በየዘርፉ የተጀመሩ ጥረቶች የሚያበረታቱና ለውጥ እየታየባቸው መሆናቸውን ገልጸዋል። ጅምሩ መጠናከር አለበት ብለዋል። እንደሀገር ተስፋ ሰጪ ዕድገት መኖሩን ጠቀመው የሚቀረን ነገር ላይ ተጨባጭ ለውጥ ለማምጣት ተባብረን መስራት አለብን ብለዋል።

በተለይም ምርታማነትን፣ ሰላምን፣ የኑሮ ሁኔታን እንዲሁም የስራ ዕድል ፈጠራ ላይ ትኩረት ተሰጥቶ መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል። እንደመንግስት ሰራተኛም በተለይ በማህበራዊ ዘርፍ ባሉ የማይክሮ ዘርፍ እቅዶችን ለማሳካት ሁሉም ‘ከእኔ ምን ይጠበቃል’ የሚለውን መፈተሽ፤ ለበለጠ ስራና ለተሻለ ውጤታማነት በእልህና በቁጭት መነሳሳትና መትጋት ይጠበቅብናል ሲሉ በአጽዕኖት አሳስበዋል።

Please follow and like us: