21ኛው ቅድሚያ ለሴቶች የ5 ኪሎ ሜትር የሩጫ ውድድር ተካሄደ

21ኛው ቅድሚያ ለሴቶች የ5 ኪሎሜትር የሩጫ ውድድር ዛሬ ተካሂዷል።

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የሚያዘጋጀውና ሴቶች ብቻ የሚወዳደሩበት የ5 ኪሎ ሜትር የሩጫ ውድድር ነው፡፡የ2016 ሳፋሪኮም ቅድሚያ ለሴቶች የሚል መጠሪያ በተሰጠው የሩጫ ውድድር 16 ሺህ ሴቶች ተሳትፈውበታል፡፡

“የሴቶችን አቅም እንደግፍ፤ ለውጥን እናፋጥን “በሚል መሪ ሃሳብ በተደረገው ውድድር የተካፈሉ ተሳታፊዎች ቁጥር በውድድሩ ታሪክ ከፍተኛው መሆኑ ተገልጿል፡፡በውድድሩ ላይ ከሀገር ውስጥ በተጨማሪ ከተለያዩ ሀገራት የመጡ ከአርባ በላይ ሴቶች መሳተፋቸው ታውቋል፡፡

በማስጀመሪያ መርኃ-ግብሩ ላይ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ፣ ሻለቃ ኃይሌ ገብረስላሴ የአዲስ አበባ ከተማ ባህልና ስፖርት ቢሮ ሃላፊ ዶክተር ሂሩት ካሰው፣ አትሌት መሰረት ደፋርና ሌሎችም ታዋቂ ግለሰቦች ተገኝተዋል።በውድድር ጉታኒ ሻንቆ 1ኛ፣ ብርነሽ ደሴ 2ኛ ፣ መቅደስ ሽመልስ 3ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቅቀዋል ሲል የዘገበው ኢዜአ ነው፡፡

 

 

Please follow and like us: