በሰላም ግንባታ ውስጥ ለሴቶች እድል መስጠት ውጤታማ እንደሚያደርግ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ሁሪያ አሊ ተናገሩ።

የአሜሪካ ኤምባሲ  “ሴቶችን በፖለቲካዊ ሂደት ማካተትንና ተሳትፎን ማሳደግ” በሚል ርዕስ የልምድ ልውውጥ እና ትስስር መድረክ አካሂዷል። መድረኩ የሴቶች ታሪክ ወር እና የአሜሪካ እና የኢትዮጵያ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት 120ኛ አመት ምክንያት በማድረግ ሴቶችን በፖለቲካዊ ሂደት ማካተትንና ተሳትፎን ማሳደግ ላይ ተኩረቱን ያደረገ ነው።

በፓናል ውይይቱ ላይ የተሳተፉት በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የማህበራዊ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ከብርት ሁሪያ አሊ በሰላም ግንባታ ውስጥ ለሴቶች እድል መስጠትና ማሳተፍ ውጤታማ እንደሚያደርግ ተናግረዋል። ሴቶች በአመራርነትና በኢትዮጵያ መደበኛ የፖለቲካ ሂደት ውስጥ እንዲሳተፉ እድሉ ሊሰጣቸው ይገባል ያሉት ክብርት ሚኒስትር ዴኤታዋ መንግስት የሴቶችን የፖለቲካ ተሳትፎና አመራር ሰጪነት ሚናን ለማሳደግ የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ ስለመሆኑ አብራርተዋል።

ክብርት ሚኒስትር ዴኤታዋ ወደ አመራርነት የመጡበትን ሂደት፣ ሴቶች በአመራርነት ወቅት ስለሚገጥማቸው ችግር እና በሰላም ግንባታ ስለሚኖራቸው ሚና ልምዳችውን አካፍለዋል።

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ክብርት ሜላትወርቅ ኃይሉ በበኩላቸው ሴቶች በፖለቲካው ዘርፍ ንቁ ተሳታፊ ቢሆኑ ከራሳቸውም አልፈዉ ሀገር መጥቀም እንደሚችሉ  ተናግረዋል።

በዝግጅቱ  የተለያዩ ተቋማት  ሴት አመራሮች ፣ ከፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ከሲቪክ ማህበራት፣ ከግሉ ሴክተር እና በትምህርት ዘርፍ ላይ የሚገኙ ሴቶች ተሳትፈዋል።

 

Please follow and like us: