በሳውዲ አረቢያ የተለያዩ ማቆያ ጣቢያዎች የሚገኙ ዜጎችን ወደ ሀገር  የመመለስ ሥራ ዳግም ተጀምሯል።

በሳውዲ አረቢያ ማቆያ ጣቢያዎች የሚገኙ ኢትዮጵያውንን ወደ ሀገር ቤት የመመለሱ ስራ ዛሬ አርብ ሚያዚያ 04 ቀን 2016 ዓ.ም የተጀመረ ሲሆን 70 ሺህ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ ታቅዷል። በእለቱ በሁለት ዙር በተከናወነ በሳውዲ አረቢያ በችግር ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን የመመለስ ስራ 823 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው መመለስ  ተችሏል።

በሳኡዲ አረቢያ እስር ቤት የሚገኙ ሰነድ አልባ ዜጎችን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ ለተከታታይ አራት ወራት በሳምንት 12 የአውሮፕላን በረራ እንደሚደረግ ተገልጿል። ከመጋቢት 21 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ በተለያየ ጊዜ በተሰራ ስራ ከመቶ አርባ ሺህ በላይ ዜጎችን ወደ ሀገር በመመለስ ለተመላሽ ዜጎች በኤርፖርትና በማቆያ ማእከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ስራ በቅንጅት መሰራቱ ይታወሳል።

 

Please follow and like us: