በሲዳማ ክልል የማህበራዊ አገልግሎት እየሰጡ የሚገኙ ባለሙያዎች ያሉበትን አጠቃላይ ሁኔታ የሚያሳይ የዳሰሳ ጥናት እንደሚካሄድ ተገለጸ፡፡

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በሲዳማ ክልል በሚካሄደው የማህበራዊ ባለሙያዎችን አሁናዊ ሁኔታ የሚመለከት የዳሰሳ ጥናት ለመረጃ ሰብሳቢ በለሙያዎች እና አስተባባሪዎች በመረጃ መሰብሰቢያ መሳሪያዎች ዙሪያ ከክልል፣ ከወረዳና ከዞን ለተውጣጡ ማህበራዊ ባሙያዎች ሥልጠና ለመስጠት ያለመ መድረክ አዘጋጅቷል።

በመድረኩ ላይ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የማህበራዊ ጥበቃ ፕሮግራሞች አስተባባሪ የሆኑት አቶ ቴዎድሮስ ሹመት ባስተላለፉት መልዕክት የማህበራዊ እድገትን ለማስቀጠል መንግስት የማህበራዊ ጥበቃ ፖሊሲን ጨምሮ በርካታ የአሰራር ማዕቀፎችን በማውጣትና ፕሮግራሞችን በመዘርጋት የተለያዩ እርምጃዎችን በመውሰድ ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል። ሆኖም ውጤታማና የተጠናከረ የማህበራዊ ጥበቃ ሥርዓት ለመዘርጋትና አገልግሎቱን በየደረጃው ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች በአግባቡ ተደራሽ ለማድረግ መዋቅሩን እስከታችኛው የአስተዳደር ዕርከን ድረስ መዘርጋት እና በበቂ የሰው ሃይል ማደራጀት አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል። የማህበራዊ አገልግሎት እየሰጡ የሚገኙ ባለሙያዎች ያሉበትን አጠቃላይ ሁኔታ የሚያሳይ (Social services workforce mapping and assessment) የዳሰሳ ጥናት ቀደም ሲል በአማራ፣ ኦሮሚያ፣ ጋምቤላ፣ ሱማሌና አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መካሄዱን ገልጸዋል።

የዳሰሳ ጥናቱ በአይነቱ የመጀመሪያ እንደሆነ የጠቁሙት ኃላፊው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን ጨምሮ በተዋረድ በሚገኙ አደረጃጀቶች እንዲሁም ሌሎች የሴክተር መ/ቤቶች እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ውስጥ ተቀጥረው ድሃና ተጋላጭ ለሆኑ የሕብረተሰብ ክፍሎች አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኙ የማህበራዊ ባለሙያዎችን ነባራዊ ሁኔታ ይዳስሳል ብለዋል፡፡

አክለውም የዳሰሳ ጥናቱ ከሲዳማ ክልል በተጨማሪ በቀሪዎቹ ክልሎችና የከተማ አስተዳድሮችም ደረጃ በደረጃ ለማካሄድ ዕቅድ መያዙንና ዩኒሴፍ ኢትዮጵያ ለዳሰሳ ጥናቱ የፋይናንስና የቴክኒክ ድጋፍ እያደረገ እንደሆነ ተገልጿዋል፡፡የሲዳማ ክልል የሴቶች፣ ወጣቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ምክትል ቢሮ ኃላፊ እና የማህበራዊ ጉዳይ ዘርፍ ኃላፊ ክቡር አቶ ባንታየሁ ቀጸላ በበኩላቸው የሚካሄደው የዳሰሳ ጥናቱ በክልሉ ውሰጥ በተለያዩ ተቋማት ውስጥ ደሃና ተጋላጭ ለሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን አገልግሎት ለመስጠት እንዲያስችሉ የተፈጠሩ የስራ መደቦችን የተጠቃለለ መረጃ ለማወቅ እንደሚረዳ ገልፀዋል፡፡

Please follow and like us: