ፆታን መሰረት ያደርገ ጥቃትን ለመከላከልና ምላሽ ለመስጠት የተዘጋጀ የአሰራር ስርዓት ይፋ ሆነ

በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ አስተተባባሪነት ፆታን መሰረት ያደርገ ጥቃትን ለመከላከልና ምላሽ ለመስጠት የአሰራር ስርዓት ተዘጋጅቶ የፌደራልና የክልል ባለድርሻ አካላትን ባሳተፈ መልኩ ይፋ ሆንዋል።

በዕለቱ የመክፈቻ ንግግር ያረጉት በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በሚኒስቴር ዲኤታ ማእረግ የሚኒስቴር አማካሪ አቶ ጌታቸው በዳኔ እንደገለፁት ጾታዊ ጥቃት እንደ ሀገር ሰፊ ችግር መሆኑን ገልጸዋል ።ሚነነስትር መስሪያቤቱም ይኽንን ችግር ለመቅረፍ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር የቅንጀት ስራዎችን እየሰራ እንደሆነ ተናግረዋል ።ከዚህም መካከል ዛሬ ይፋ የተደረገው ፆታን መሰረት ያደርገ ጥቃትን ለመከላከልና ምላሽ ለመስጠት የተዘጋጀው የአሰራር ስርዓት አንድ መሆኑን ጠቅሰዋል።ይህ የአሰራር ስርአትም ኢትዮጵያ ፆታን መሰረት ያደርገ ጥቃትን ለመከላከልና ምላሽ ለመስጠት ያላትን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ሲሆን የምንሰራውንም ስራ ለማሳለጥ ይረዳል ብለዋል። አክለውም ይህን የአሰራር ስርዓቱ የሚመለታቸው አካላት ወስደው በባለቤትነት መተግበር እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡

በስነ ስርዓቱ ላይ ላይ በመገኘት በፕሮግራሙ መልእክት ያስተላለፍት በኢትዮጵያ የ ዩኤን.ኤፍ.ፒ.ኤ (UNFPA) ምክትል ተወካይ ታይዎ ኦሉዮሚ የአሰራር ስርዓቱ እንደ ሀገር ፆታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶችን ለመከላከልና ግልጽ እና ደረጃቸውን የጠበቁ አሰራሮችን በመዘርጋት መከላከል እና ምላሽ አገልግሎቶችን ጥራት እንደሚያጎለብት ጠቅሰዋል። አክለውም በአሰራር ስርዓቱ ዝግጅት ወቅት የተሳተፍትን አመስግነዋል፡፡በመጨረሻም የእለቱ የክብር እንግዶች የጤና ሚኒስቴርና የፍትህ ሚኒስቴር ዲኤታዎችን ጨምሮ በተዘጋጀው የአሰራር ስርዓት ላይ ፊርማቸውን በማስቀመጥና በጋራ ለመተግበር ሃላፊነትን በመውሰድ የአሰራር ስርዓቱን ይፋ አድርገዋል፡፡

ፆታን መሰረት ያደርገ ጥቃትን ለመከላከልና ምላሽ ለመስጠት የተዘጋጀውን የአሰራር ስርዓት ለማዘጋጀት የተሄደበት ሂደትን ፣የአሰራር ስርዓቱ ምን ምን ነገሮችን እንደያዘ የሚገልፁ ትንታኔዎች በሚኒስቴር መ/ቤቱ የሴቶች ጥቃት ጥበቃና ምላሽ ዴስክ የዘርፉ ባለሙያዎች ቀርቧል፡፡

Please follow and like us: