ዩኒ ሴፍ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸውን ዜጎች ለመደግፍ የሚያስችል የ5 አመት ፕሮግራም ቀርፆ ወደ ስራ ሊገባ ነው።

በሚቀጥሉት 5 ዓመታት ውስጥ በመላ ሀገሪቱ ሴቶች፣ ህጻናት እና ወጣቶችን ጨምሮ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸውን ዜጎች ህይወት ለማሻሻል ቅድሚያ በሚሰጣቸው ጉዳዮች ላይ የጋራ ግንዛቤ መፍጠር የሚያስችል ውይይት ተካሂዷል። ፕሮግራሙ በሴቶች ማብቃትና መብት ፣ በወጣቶች ልማት፣ በህጻናት መብትና ጥበቃ፣ በአረጋውያን እንክብካቤ እና የአካል ጉዳተኞች ድጋፍ ላይ ያተኮረ ነው።

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ሁሪያ አሊ ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች የሚያጋጥሟቸውን ዘርፈ ብዙ ችግሮች ለመፍታት የጋራ ጥረት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል። ዩኒሴፍ የነደፈው ፕሮግራም በበርካታ ዜጎች ህይወት ላይ አዎንታዊ ለውጥ ለማምጣት ያስችላል ያሉት ክብርት ሚኒስትር ዴኤታዋ አካታች የሆነና ማንንም ወደ ኋላ የማያሰቀር የማህበረሰብ ለውጥ ለማምጣት በትኩረት መስራት ይገባል ብለዋል።

በሁሉም ደረጃ ያለውን ሁለንተናዊ የአቅም ግንባታ ፍላጎቶች ለማሟላት የዩኒሴፍ የሀገር ልማት ፕሮግራም እንደ አንድ ንዑስ ፕሮግራም እንዲሆንም ጠይቀዋል። በተጨማሪም ባለፉት አምስት አመታት የተሰሩ ስራዎችን በUNICEF የፕሮግራሙ ሀላፊዎች አቅርበዋል ::

የሚኒስትር መ/ቤቱ የስራ ክፍል ሀላፊዎች በቀጣይ አምስት አመት ፕሮግራሙ ሊያቅፋቸው የሚገቡ ስትራቴጂያዊ ጉዳዮችን አቅርበዋል ። በቀጣይ አቅዱን በቅንጅት የማዘጋጀት ስራ ይከናወናል።

Please follow and like us: