1 ሺህ 190 ኢትዮጵያውያን ከሳውዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።

በሶስት ዙር በረራ በተከናወነ በሳውዲ አረቢያ በችግር ውስጥ የነበሩ ዜጎችን የመመለስ ስራ 1 ሺህ 190 ኢትዮጵያውያንን ትናንት ወደ ሀገራቸው መመለስ ተችሏል።

በዛሬው እለት ወደ ሀገር የተመለሱት 1 ሺህ 190 ዜጎች ሁሉም ወንዶች  ሲሆኑ 7  እድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ናቸው። ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡

የኢፌዴሪ መንግስት በሰራው ዜጋ ተኮር ጠንካራ የዲፕሎማሲ ስራ ከሚያዚያ 04 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እስካሁን ከ6600 በላይ ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገር መመለስ ተችሏል ።

Please follow and like us: