1 ሺህ 206 ኢትዮጵያውያን ከሳውዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

በሶስት ዙር በረራ በተከናወነ በሳውዲ አረቢያ በችግር ውስጥ የነበሩ ዜጎችን የመመለስ ስራ 1 ሺህ 206 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው መመለስ ተችሏል።

በዛሬው እለት ወደ ሀገር ከተመለሱት 1 ሺህ 206 ዜጎች ውስጥ 994 ወንዶች፣ 172 ሴቶች፣ 6 እድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች እና 40 ጨቅላ ህፃናት ናቸው። ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡ የኢፌዴሪ መንግስት በሰራው ዜጋ ተኮር ጠንካራ የዲፕሎማሲ ስራ ከሚያዚያ 04 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እስካሁን ከ7800 በላይ ኢትዮጵያውያንን መመለስ ተችሏል።

Please follow and like us: