በአፋር ክልል ከ10 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጣው የሰው ሰራሽ የአካል ድጋፍ (Prosthetic Orthotics)  አገልግሎት የማስጀመሪያ መርሃ ግብር ተካሂዷል። 

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከህንድ መንግስትና ኢትዮጵያ ከሚገኘው የህንድ ኢምባሲ ጋር በመተባበር በአፋር ክልል ለሚገኙ  በተለያዩ ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ አደጋዎች የአካል ጉዳት ለደረሰባቸው ሰዎች የሰው ሰራሽ አካል ድጋፍ ማስጀመሪያ መርሃግብር በ ሎጊያ ከተማ አካሄደ፡፡

በማስጀመሪያ መርሀ ግብሩ ላይ የተገኙት የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ተወካይና የአካል ጉዳተኞች  ጉዳይ መሪ ሰራ አሰፈጻሚ አቶ አሳልፈው አመዲን እንደገለፁት ለ 400 አካል ጉዳተኞቾ ይህ የአካል ድጋፍ መደረጉ ከቦታ ቦታ የመንቀሳቀስ ተግዳሮታቸውን እንዲፈቱ ከማሰቻሉም በላይ ነፃነታቸው እና ክብራቸውን ተመልሶ   በማህበረሰቡ ውስጥ ተገቢዉን ተሳትፎ እንዲያደርጉ ትልቅ እድል ይሰጣል  ብለዋል።

አክለውም ይህ አይነቱ ድጋፍ በኢትዮጵያ እና በህንድ መካከል ያለውን ዘላቂ ወዳጅነት እና ትብብር አጉልቶ እንደሚያሳይ ጠቅሰው ሚኒስትር መስሪያ ቤቱም ቃሉን በተግባር ያሳየበት ስራ መሆኑን ጠቅሰዋል።

በኢትዮጵያ የህንድ አምባሳደር ሚስተር አኒል ኩማር ራኢን በበኩላቸው በህንድ መንግሥት  በኩል የሚሰጠው የዚህን አይነቱ ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸው በአፋር ክልል ለሚገኙ አመራሮችና ባለሙያዎቾም የእውቀት ሽግግርና የአቅም ማጎልበቻ ስልጠናዎች ቀጣይነት ባለው መልኩ ለመስጠት ኤምባሲው ሁኔታዎችን እንደሚያመቻች ቃል ገብተዋል ።

 

አገልግሎቱ ከህንድ በመጡ 8 የህክምና ባለሙያዎች እና በሰመራ ዩኒቨርሰቲ ሎጊያ ሆስፒታል ባለሙያዎች በትብብር 400 ለሚሆኑ ወገኖች  ለቀጣዮቹ 50 ቀናት  እንደሚሰጥ ተገልጿል።

በማስጀመሪያ ስነ-ስርዓቱ ላይም የሠመራ ዮኒቨርሲቲ ኘሬዚደንት ፣ የአፋር ክልል መንግስት ተወካይ ፣ የክልሉ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ፣ የክልል ጤና ቢሮ ምክትል  ሀላፊ ፣ ፕሮግራሙን ላለፉት ስምንት አመታት ሲያስተባብሩ የቆዩት ፕሮፌሰር ባሳር እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች፣ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ አካል ጉዳተኞቾ እና ቤተሰቦቻቸዉ ተገኝተዋል ።

 

Please follow and like us: